የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ መጽሐፍ

- Advertisement -
Sidebar AD

“ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ይመረቃል

#Ethiopia | የጋዜጠኛ፣ ደራሲና መምህር ዐቢይ ይልማ አምስተኛ መጽሐፍ የሆነው “ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል።

መጽሐፉ በዘመናችን በብዙ ሰዎች የሚስተዋሉ እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የባዶነት ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ሱሰኝነት፣ የገንዘብ ችግርና ሌሎች የሕይወት ፈተናዎች ዙሪያ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ እይታዎችን በማቀናጀት ለአንባቢያን ተስፋና መነሳሳት ለመስጠት ያለመ ሥራ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ደራሲው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ያጋጠሙትን ለ12 ዓመታት የዘለቀ ከባድ የጤናና የሕይወት ፈተና በድል ካለፉ በኋላ ያገኙትን ልምድና እውቀት በዚህ መጽሐፍ አካፍለዋል።

አዘጋጅ ኮሚቴው በዕለቱ የሚካሄደውን የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት እንዲታደሙ የደራሲውን ወዳጆች፣ የሥነ ጽሑፍ አፍቃሪዎችና መላውን ሕዝብ በክብር ጋብዟል።

ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም.
ጠዋት 4፡00 ሰዓት
ቦሌ ዓለም ሲኒማ

እንኳን ወደ መጽሐፉ ምረቃ በደህና መጡ!


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: