#Ethiopia | የጉግል ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ሱንዳር ፒቻይ ከ2026 እስከ 2030 ያሉት ዓመታት ተራው ሕዝብ በከፍተኛ ደረጃ ሀብት ለማፍራትና የኢኮኖሚ አቅሙን ለማሳደግ የሚያገኝበት የመጨረሻው ወርቃማ አጋጣሚ መሆናቸውን ገለጹ።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በሰጡት ማብራሪያ በአሁኑ ወቅት እየታየ ያለው የቴክኖሎጂ እና የኢኮኖሚ ሽግግር ለብዙዎች ያልተጠበቀ የሀብት ፈጠራ ዕድል ይዞ የመጣ ቢሆንም ይህን አጋጣሚ አሁኑኑ ተፎካካሪ ሆኖ ያልተጠቀመበት የሕብረተሰብ ክፍል ግን ወደፊት የሚፈጠሩትን እድሎች ለማግኘት እጅግ እንደሚቸገር አሳስበዋል።
በመሆኑም ሰዎች አዳዲስ የስራ አዝማሚያዎችን ቀድመው በመገንዘብ አሁኑኑ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉና ይህን አጋጣሚ ወደ እውነተኛ ስኬት እንዲቀይሩት ጥሪ የቀረበ ሲሆን ትክክለኛውን እርምጃ በአሁኑ ወቅት መውሰድ የነገውን የገንዘብ ነፃነት ለመወሰን ወሳኝ መሆኑ ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.