የ112 ፍልስጤማውያን የቀብር ስነ ስርዓት በዛሬው እለት አንድ ላይ ተፈጸመ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በ2023 በእስራኤል ወታደራዊ ጥቃት ህይወታቸውን ያጡ በወቅቱ አስከሬናቸው ያልተመለሰ 112 ዜጎች ስርአተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

112 የፍልስጤማዊያን አስከሬኖች በቅርቡ በተደረገው ስምምነት መሰረት እስራኤል የመለሰች ሲሆን አብዛኞቹ አስከሬኖች ማንነታቸው በውል አይታወቅም ተብሏል።

አስክሬኖቹ ማንነታቸው ለማወቅ ባለመቻሉ እና ሙሉ በሙሉ መለየት ሳይቻል የቀሩ በመሆናቸው በጋዛ በይፋ በጋራ እንዲያርፉ ተደርጓል ሲል አልጀዚራ ፅፏል።

ከዚህ በተጨማሪም አስከሬኖቹ በእስራኤል ጦር ተይዘው ከቆዩ በኋላ የተመለሱ ቢሆንም የበርካቶቹ ማንነት ሳይለይ በመቅረቱ በቁጥር እና በመለያ ምልክቶች ብቻ ተመዝግበው እንዲያርፉ ተደርጓል ብሏል።

በሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች እና የሟች ቤተሰቦች በቀብር ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችም የሟቾችን አስከሬን ይዞ ማቆየት ህገ ወጥ መሆኑን በመግለጽ ድርጊቱን ኮንነውታል።

የጋዛ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው አሁንም በሺዎች የሚቆጠሩ የፍልስጤማውያን አስከሬን በፍርስራሾች ስር እንደሚገኝ ገልጿል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Gaza #MassFuneral
#Sabraattack


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: