#Ethiopia | አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር – አድማስ ሁለገብ የገበሬዎች የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዩኒየን በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የተሻሻሉ የድንች ዘሮችን በማባዛት የአርሶ አደሮችን ምርታማነትና ገቢ ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን ገለጸ።
በአንከሻ ጓጉሳ ወረዳ ካፍታ ቀበሌ 20 ወጣቶች በሚያካሂዱት የድንች ዘር ብዜት ልማት ላይ የገበሬዎች በዓል ተካሂዷል።
የዩኒየኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሠረት ወርቄ፣ በአካባቢው የድንች ምርጥ ዘር እጥረትን ለመቅረፍ የተሻሻሉ ዘሮችን የማባዛት ሥራ መጀመሩን ገልጸው፣ ከ1.5 ሄክታር የተጀመረው ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት በ6 ሄክታር መሬት በጓንጓ፣ ባንጃ፣ አንከሻ እና ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳዎች መስፋፋቱን ጠቁመዋል።
እንደ መሠረት ወርቄ ገለጻ፣ ዩኒየኑ በቀጣይ ዓመት የዘር ብዜት ልማቱን ወደ 15 ሄክታር በማስፋት የድንች ሰብልን ከምግብነት ባለፈ ለኢንዱስትሪ ግብዓት እንዲሆን ለማድረግ እየሰራ ነው።
የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ ቤዛዊት ጌታሁን በበኩላቸው፣ ድንች ለምግብ ዋስትና ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ ዕድገትም ጠቃሚ ሰብል መሆኑን ገልጸው፣ የተሻሻሉ ዝርያዎችን ማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
“በለጠ” የተሰኘው የድንች ዝርያ በሽታን የመቋቋም አቅም ያለው ሲሆን፣ በሄክታር እስከ 350 ኩንታል ምርት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.