ኢትዮጵያ ያልተጠቀመችበት ድብቅ ወርቅ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ካሳቫ (Cassava) ከቁልቋል (Euphorbiaceae) ቤተሰብ የሚመደብ ሲሆን ከ200 በላይ ዝርያዎች አሉት፡፡

በ16ኛው ክፍለ ዘመን በፖርቱጋል ነጋዴዎች አማካኝነት ወደ ምዕራብ አፍሪካ እንዲሁም በ18ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ደግሞ ወደ ምስራቅ አፍሪካ እንደገባ መዛግብት ያመለክታሉ፡፡

ካሳቫ ማዳበሪያ የማይፈልግ፣ ወፍና ተባይ፣ ጦጣና ዝንጀሮ የማይበላው፣ መሬት ውስጥ ሁለት ዓመታት ቢቆይ የማይበላሽ፣ ብዙ እንክብካቤ የማያስፈልገው፣ በተመናመነና በአሲዳማ መሬት እንኳ ከፍተኛ ምርት መስጠት የሚችል፣ ከፍተኛ ድርቅ/ኢሊኖን የመቋቋም አቅም እና አስደናቂ ተፈጥሯዊ ብቃት ያለው “የጽናት ሰብል” በመባል የሚታወቅ ተክል ነው፡፡

ካሳቫ በውስጡ ከፍተኛ የካርቦሃይድሬት ይዘት ስላለው በሃይል ሰጪነቱ ከሥራሥር ተክሎች ሁሉ ተወዳዳሪ የሌለዉ ሲሆን፣ ተቀቅሎ ከመበላቱም በላይ ደርቆና ተፈጭቶ እንደ ጤፍ ካሉ ሌሎች እህሎች ጋር ለእንጀራ፣ ለብስኩት፣ ቂጣ፣ ገንፎ፣ ወጥ እና ለሾርባ ዝግጅት ይውላል።

የስሩ ተረፈ-ምርት እና በፕሮቲን የበለጸገው ቅጠሉ ደግሞ ለእንስሳት መኖ ያገለግላል፡፡

ከዚህ ባሻገር ለጨርቃጨርቅ፣ ለወረቀት፣ ለመድኃኒት፣ ለምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ዋነኛ ግብዓት ነው።

ካሳቫ ከባህር ወለል በላይ ከ0-4000 ሜትር ከፍታ በሁሉም የኢትዮጵያ ሥነ ምህዳር መልማት የሚችል ሲሆን እንደ ደቡብ ኢትዮጵያ ባሉ ክልሎች ለምግብነት ያለዉ ተፈላጊነት እየጨመረ መጥቷል፡፡

ሥሩ በመሬት ውስጥ ተደብቆ የሚለማው ካሳቫ በብዙ የሀገሪቱ ክፍሎች በብዛት ሳይለማ ተደብቆ ያለ ሰብል ነው፡፡

የካሳቫን እምቅ አቅምና አዋጭነት ከግምት ውስጥ በማስገባት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶአደሮች እና ባለሀብቶች ብሎም በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት ይህን የተደበቀ ሀብት ማውጣት ይገባቸዋል።

የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥና ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የወደፊቱ ዋነኛ የኤክስፖርት ምርት በማድረግ የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ በጥናት የተመሰረቱ ስልቶች እየተቀየሱ ይገኛሉ፡፡

በዚህም የካሳቫ ኮንትራት አምራቾችና ኤክስፖርተሮች ማህበር ልማቱን በማስፋፋት ምርቱን በችብስ መልክ በማዘጋጀት ወደ ውጭ ለመላክ ቅድመ ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡

ግብርና ሚኒስቴር

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#ኢትዮጵያ #ግብርናሚኒስቴር
#ካሳቫ #የምግብዋስትና
#ምርምር #ግብርና


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1