#Ethiopia | የኳታሩ አሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ የአገልግሎት ዘመናቸውን ያጠናቀቁትን የኢትዮጵያ አምባሳደር ፊሰል አሊ ኢብራሂምን፣ የጋና አምባሳደር መሐመድ ኑሩዲን እስማኤልን እና የስዊድን አምባሳደር ጓታም ኤስ. ብሃታቻርያን በሉሳይል ቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው አናግረዋል።
አሚሩ ዲፕሎማቶቹ ከኳታር ጋር የነበራቸውን የሁለትዮሽ የትብብር ግንኙነት ለማጠናከር ላበረከቱት አወንታዊ አስተዋጽኦ እውቅና በመስጠት የ’አል ወጅባ’ (የክብር ሽልማት አበርክተውላቸዋል።
በተጨማሪም ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አል ታኒ ለአምባሳደሮቹ በቀጣይ የሥራ ምዕራፋቸው ስኬትን የተመኙ ሲሆን በኳታርና በየሀገራቸው መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ እየጎለበተ እንዲሄድ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.