በጋዜጠኛ ብሩክ ተስፋዬ
#Ethiopia | ዛሬ በሚጀምረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተፈጠሩት ነገሮች ምንድን ናቸው የስፖርት ቤተሰብ አወዛግቧል ለምን ?
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለተሳታፊ አትሌቶችና አሰልጣኞች ቪዛ እንዲገኝ ልዩ ክትትል በማድረግ የቆየ ቢሆንም፣ በመጨረሻ 7 አትሌቶች ቪዛ ቢኖራቸውም ከጉዞው መቅረታቸው ታውቋል።
በእነዚህ ውስጥ የአትሌት አጀይባ አልዬ ጉዳይ በተለይ ትኩረት ስቧል። እስካሁን ከወርልድ አትሌቲክስ የተለየ ይፋዊ ማብራሪያ ስላልቀረበ፣ አትሌቷ ወደ ውድድሩ ስፍራ አልተጓዘችም። በእንዲህ ዓይነት ጉዳዮች የመጨረሻ መረጃ ሳይገኝ የግለሰብን ስም እየጠቀሱ መደምደሚያ መስጠት ተገቢ እንዳልሆነ የወርልድ አትሌቲክስ ህግ ያስቀምጣል። ስለዚህ ይፋዊ ምላሽ እስኪገኝ ድረስ ጉዳዩ ግልጽ ማብራሪያ ይፈልጋል።
በሌላ በኩል፣ የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና የካሜራ ባለሙያ ወደ ውድድሩ ስፍራ አልተጓዙም። ምክንያቱም ቪዛ ባለማግኘታቸው ሲሆን፣ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የውስጥ ደንብ መሠረት ለቢሮ ሠራተኞችና ለሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለአሜሪካ ኤምባሲ የቪዛ ሂደት የሚፈለግ ማንኛውንም የቦንድ ክፍያ ፌዴሬሽኑ እንደማይሸፍን በተቀመጠው የውስጥ ደንብ መሠረት ነው።
“7 አትሌቶች ለምን ቀሩ?” ለሚለው ጥያቄ እስካሁን ባገኘነው መረጃ መሠረት፣ አንዷ አትሌት አጃይባ አልዬ ስትሆን፣ ሌሎች ሦስት አትሌቶች ተጠባባቂ ነበሩ። ዋና ተሳታፊ አትሌቶቹ በጤና ችግር ሳይገጥማቸው በውድድሩ በመሳተፋቸው፣ ተጠባባቂዎቹ ወደ ውድድሩ ስፍራ አልተጓዙም። ቀሪዎቹ ሦስት አትሌቶች ደግሞ ሚኒማ ባለማሟላታቸው ወደ ውድድሩ ስፍራ እንዳልተጓዙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ግን እውነት ይህ ነው ከውድድር በኋላ እንመለስበታለን?
ይህ እስካሁን የደረሰን መረጃ ሲሆን፣ ጉዳዩን ከውድድሩ በኋላ በሚገኙ ይፋዊ ማብራሪያዎች መሠረት በዝርዝር እንመለስበታለን።
የዚህን የቪዛ ሂደት በቅርብ ሲከታተሉ የቆዩት የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር አመንሲሳ ከበደ ዛሬ ምሽት ወደ ውድድሩ ስፍራ አቅንተዋል።
በመጨረሻ ሰዓት የቡድን መሪው እና የቴክኒክ ሀላፊው ቪዛ ባለማግኘታቸው ምክንያት ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አትሌት መሰረት ደፋር የቡድኑ መሪ ሆኗ ወደ ስፍራው አቅንታለች ። ቀድሞውኑ የአሜሪካ ቪዛ በእጃቸው የነበረው የአሰልጣኞች ማህበር ፕሬዚዳንትና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ስፖርት ክለብ የረጅም ርቀት አሰልጣኝ ኮማንደር ቶሌራ ዲንቃም የቡድኑ የቴክኒክ ኃላፊ ሆነው ወደ ስፍራው አምርተዋል።
የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ለሊት ይጀምራል። ከፍተኛ ዝግጅትና ጥረት የተደረገበት ይህ ውድድር ከተጠናቀቀ በኋላ በተፈጠሩት ጉዳዮች ላይ ከአትሌቶች፣ ከአሰልጣኞችና ከአመራሮች በቀጥታ ማብራሪያ በማቅረብ በቻናል 1 ስፖርት የ«አትሌቲክስ ቆይታ» ፕሮግራም በዝርዝር እንመለስበታለን።
መልካም ዕድል ለመላው ለኢትዮጵያ ሀገራችን !

Source: GetuTemesgen









No comments yet.