ጅዳ የአለም ትልቁን ህንፃ እየገነባች ትገኛለች

- Advertisement -
Sidebar AD

*የህንጻው ቁመት 1 ኪሎ ሜትር ይረዝማል

*20 ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል

#Ethiopia | በሳዑዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው እና የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ ለመሆን የተቃረበው የጄሲ ህንጻ ግንባታ አጋማሽ ላይ ደርሷል።

ህንፃው በአሁኑ ወቅት የቁመቱን አጋማሽ የደረሰ ሲሆን ግንባታው ሙሉ በሙሉ ለመጨረስ እየተፋጠነ ይገኛል።

ህንፃው አጋማሽ ላይ ሲደርስ አሁን ላይ ቁመቱ 500 ሜትር ደርሷል ተብሏል።

ህንጻው 500 ሜትር ደርሶ 120ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ ከ1,000 ሜትር 1 ወይም ኪሎሜትር በላይ ቁመት ይኖረዋል።

በሳዑዲ አረቢያው ልዑል አል ወሊድ ቢን ታላል በሚመራው ኪንግደም ሆልዲንግ ገንዘብ ድጋፍ በሚደገፈው ጅዳ ኢኮኖሚክ ካምፓኒ (JEC) አማካኝነት እየተገነባ ይገኛል።

ህንፃው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ሲከፈት በአሁኑ ወቅት የዓለማችን ረጅሙ ህንፃ የሆነውን የዱባዩን ቡርጂ ካሊፋን የሚበልጥ ይሆናል።

የቡርጂ ካሊፋ ህንጻ ቁመቱ 828 ሜትር ከፍታ አለው።

የጄሲ ህንፃ የ1 ኪሎ ሜትር ቁመት ያለው ሜጋ ህንፃ በመሆን የአለማችን ቁጥር አንድ ትልቁ ህንጻ ይሆናል።

የህንፃው ግንባታ ዘመናዊ ቢሮዎችን፣ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል፣ የቅንጦት መኖሪያዎች፣ የመዝናኛ ማዕከላትና ከ2,000 በላይ ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ስፍራ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ህንጻው ሙሉ በሙሉ ገንብቶ ለማጠናቀቅ ከ20 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚወስድ ነው የተገለፀው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#SaudiArabia #Jeddah #Economiccity
#JECBuilding


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: