#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያ ወጣቶች የክረምቱን ወቅት በአግባቡ በመጠቀም በነጻ በሚሰጠው የ5 ሚሊዮን ኮደርስ (5 Million Coders) የዲጂታል ትምህርት መርሃ ግብር ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት የጥሪ መልእክት ይህ የትምህርት ዕድል ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው የምስክር ወረቀት የሚያስገኝና የሀገሪቱን ወጣቶች የቴክኖሎጂ አቅም የሚያሳድግ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እድሉን ለመጠቀም ቀድመው መወሰናቸውን በመጠቆም ወጣቶች ethiocoders.et በሚለው የበይነመረብ አድራሻ አሁኑኑ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑና የራሳቸውን ብሩህ መጻኢ ጊዜ እንዲገነቡ አሳስበዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.