#Ethiopia | በታሪክ ውስጥ ግን ይህንን ታላቅ ሽልማት ከአንድ ጊዜ በላይ በማሸነፍ የዓለምን የሳይንስና የሰላም አቅጣጫ የቀየሩ ጥቂት ድንቅ ግለሰቦች አሉ።
ፖላንዳዊቷ የፊዚክስና የኬሚስትሪ ተመራማሪ ሜሪ ኩሪ በኖቤል ታሪክ ውስጥ ትልቁን ድርሻ ትይዛለች።
ሜርኩሪ በፈረንጆቹ 1903 በፊዚክስ ዘርፍ በጨረራ ምርምሯ የመጀመሪያ ሽልማቷን ተቀብላለች።
በ1911 ደግሞ በኬሚስትሪ ዘርፍ የፖሎኒየም እና ሬዲየም ንጥረ ነገሮችን ግኘት ይፋ በማድረጓ ሁለተኛውን የኖቤል ሽልማት አሸንፋለች።
ይህ ስኬቷ በሁለት የተለያዩ የሳይንስ ዘርፎች የኖቤል ሽልማት ያገኘች የመጀመሪያዋና ብቸኛዋ ሰው አድርጓታል።
አሜሪካዊው ሳይንቲስት ሊነስ ፖሊንግ ሁለት የኖቤል ሽልማቶችን በማሸነፍ በታሪክ አይነተኛ ስፍራ ያለው ሌላኛው ሰው ነው።
በ1954 በኬሚስትሪ ዘርፍ የሞለኪውሎችን መዋቅር በመመርመር የመጀመሪያውን ሽልማት ተቀብሏል።
በ1962 ደግሞ የኑክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራዎችን በመቃወምና ለአለም ሰላም ባደረገው ከፍተኛ እንቅስቃሴ የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሁለተኛ ጊዜ ሊበረከትለት ችሏል።
አሜሪካዊው የፊዚክስ ሊቅ ጃን ባርዲን የዘመናዊው ኤሌክትሮኒክስ መሰረት በሆኑ ግኝቶቹ ሁለት ሽልማት የተቀበለ ስኬታማ ሰው ይገኝበታል።
በ1956 ዘመናዊ የኮምፒውተርና የቴክኖሎጂ አብዮትን የከፈተውን ትራንዚስተር በመፍጠሩ እንዲሁም በ1972 የሱፐርኮንዳክቲቪቲ ቲዮሪን በማውጣቱ ሁለቱንም ሽልማቶች በፊዚክስ ዘርፍ ማሸነፍ ችሏል።
እንግሊዛዊው ባዮኬሚስት ፍሬደሪክ ሳንገር በኬሚስትሪ ዘርፍ ሁለት ጊዜ የኖቤል ሽልማት ከተቀዳጁ ሁለት ሰዎች መካከል አንዱ ነው።
በ1958 የኢንሱሊን ፕሮቲን መዋቅር በመለየቱ የመጀመሪያውን ሽልማት ወስዷል።
እንደዚሁም በ1980 ደግሞ የዲ.ኤን.ኤ ቅደም ተከተል መለኪያ ዘዴን በመፍጠሩ ሁለተኛውን የኬሚስትሪ ኖቤል ሽልማት የተቀበለ ባለታሪክ ነው።
አሜሪካዊው የኬሚስትሪ ተመራማሪ ባሪ ሻርፕለስ በ2022 ሁለተኛ የኖቤል ሽልማቱን በማሸነፍ የዚህ የክብር ስብስብ አምስተኛው አባል መሆን የቻለ ግለሰብ ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nobelprize
#Science #Physics
#chemistry #technology
Source: GetuTemesgen








No comments yet.