ሶሎሞን ዘውዱ ዳምጤ ለ2ኛው የአዲስ አበባ መስተንግዶና ቱሪዝም እውቅናና ሽልማት እጩ ሆነው ተመረጡ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የሆስፒታሊቲ ክላስተር ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሶሎሞን ዘውዱ ዳምጤ ለ2ኛው የአዲስ አበባ መስተንግዶና ቱሪዝም እውቅናና ሽልማት (2nd Addis Ababa Hospitality & Tourism Award & Recognition) በይፋ እጩ ሆነው ተመርጠዋል።

ሶሎሞን ዘውዱ ዳምጤ በ”Hospitality Executive Leader Excellence Recognition” ዘርፍ በAAHTPA-036 የእጩ መለያ ቁጥር ተወዳዳሪ ሆነው ቀርበዋል።

ይህ እውቅና በኢትዮጵያ የመስተንግዶ ዘርፍን በራዕይ፣ በአመራር ብቃት እና በተቋማዊ ልህቀት የሚያበረታቱ መሪዎችን ለማክበር የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

የሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. (ኦገስት 29፣ 2026) በአዲስ አበባ በካፒታል ሆቴል እና ስፓ ይካሄዳል።

አዘጋጆቹ የመስተንግዶና ቱሪዝም ዘርፍ ባለሙያዎችንና ህዝቡን ለሶሎሞን ዘውዱ ዳምጤ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት በማስተላለፍ ድጋፋቸውን እንዲገልጹ ጥሪ አቅርበዋል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: