እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሐዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ገብርኤልና አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ እግዚአብሔርን ያገለገለ፤ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፤ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፤ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅዱስ፡፡ ዮሐንስ ማለት እግዚአብሔር ጸጋ ነው ማለት ነው፡፡ በሉቃስ 1÷14 እንደተጻፈው ቅዱስ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስን ተድላና ደስታ ይለዋል፡፡ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና፡፡ በዚህ የወንጌል ክፍል ካህኑ ቅዱስ ዘካርያስና ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ሁሉ በመፈጸም ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ፡፡ ኤልሳቤጥም መካን ነበረችና ልጅ ይሰጣቸው ዘንድም እግዚአብሔርን ዘወትር ይማጸኑት ነበር፡፡ ካህኑ ዘካርያስ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ ዕጣን በማሳረግ ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ በዕጣኑ መሠዊያ ቀኝ ቆሞ ጸሎቱ እንደ ተሰማ ነገረው፡፡

ሚስቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ እንደምትወልድ፣ ስሙንም ዮሐንስ እንደሚለው፤ በመወለዱም ብዙዎች እንደሚደሰቱ፤ ልጁም በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ እንደሚኾን፤ የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ እንደማይጠጣ፤ እንደዚሁም ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ እንደሚሞላበት ነገረው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም መልአኩን “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም አርጅታለችና ይህን በምን አውቃለሁ?” አለው፡፡ መልአኩም “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፡፡ እነሆም በጊዜው የሚፈጸመውን ቃሌን ስላላመንህ ይህ ነገር እስከሚኾን ቀን ድረስ ዲዳ ትሆናለህ፤ መናገርም አትችልም” አለው፡፡ ከውጪ ቆመው ጸሎት ሲያደርጉ የነበሩት ሕዝብም ዘካርያስን ከቤተ መቅደስ እስኪወጣ ይጠብቁት ነበር፤ በመዘግየቱም ይደነቁ ነበር፡፡

ከቤተ መቅደስ በወጣም ጊዜ ሊያናግራቸው ባለመቻሉ ይጠቅሳቸው ነበር፡፡ በሁኔታውም በቤተ መቅደስ ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፡፡ እርሱም ድዳ ሆኖ ኖረ፡፡ የማገልገሉም ወራት ሲፈጸም ወደ ቤቱ ሔደ፤ ከሁለት ቀን በኋላም አረጋዊቷ ቅድስት ኤልሳቤጥ ፀነሰች፡፡ ቅድስት ኤልሳቤጥም በመካንነቷ ከሰዎች የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዷላታልና “እግዚአብሔር በዚህ ወራት ከሰው ስድቤን ያርቅ ዘንድ እንዲህ አደረገልኝ” ስትል ለአምስት ወራት ተሸሸገች፡፡ ጌታችን ሊወለድ ስድስት ወራት ሲቀረው፣ ሰኔ 30 ቀን ንዑድ፣ ክቡር የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ተወለደ፡፡ ዘመዶቹ ስሙን በአባቱ መጠርያ ዘካርያስ ሊሉት ቢወዱም እናቱ ግን “ዮሐንስ ይባል” አለች፡፡ የመልአኩን የብሥራት ቃል ባለመቀበሉ አንደበቱ ተይዞ የነበረው ካህኑ ዘካርያም ስሙ “ዮሐንስ” ይባል ብሎ ሲጽፍ አፉ ተከፈተ፤ አንደበቱም ተፈታ፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶም “… አንተ ሕፃን ሆይ! የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ መንገዱን ልትጠርግ በጌታ ፊት ትሔዳለህና… ብርሃኑም በጨለማና በሞት ጥላ ተቀምጠው ላሉት ያበራል፤ እግሮቻችንንም በሰላም መንገድ ያቀናል፤” በማለት የቅዱስ ዮሐንስን ነቢይነትና አጥማቂነት፣ እንደዚሁም የክርስቶስን የማዳን ትምህርት አብሣሪነት የሚመለከት ትንቢት አስቀድሞ ተናገሯል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ሰኔ 30 ቀን የተወለደበት፤ መስከረም 1 ቀን ቃል ኪዳን የተቀበለበት፤ መስከረም 2 ቀን በሰማዕትነት ያረፈበት፤ ጥር 11 ቀን ጌታችንን ያጠመቀበት፤ ሰኔ 2 ቀን ደግሞ ዐፅሙ የፈለሰበት በዓል በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ ይከበራል፡፡ የገዳማዊ ሕይወት ምሣሌ የሆነውን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ስናስብ ገዳማውያንን መደገፍ፣ በዓታቸውንም ማጽናት ይገባል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: