እግዚአብሔር ይመስገን፤ ሙሉ ጤንነት ላይ እገኛለሁ

- Advertisement -
Sidebar AD

– ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ

#Ethiopia | ተወዳጁ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ጎሳዬ ተስፋዬ ከሰሞኑ ያጋጠመውን የመውደቅ አደጋ ተከትሎ ስለ ጤንነቱ ለአድናቂዎቹ የምስጋና መልዕክት አስተላልፏል።

ድምፃዊው በመልዕክቱ እንደገለጸው፣ ሐምሌ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከለንደን ወደ ኢትዮጵያ በሚመለስበት ወቅት ያጋጠመው አደጋ ብዙ አድናቂዎቹን ለጭንቀት መዳረጉን አስታውሶ፣ በወቅቱ ላሳዩት ፍቅር፣ ድጋፍና ጸሎት ከልብ አመስግኗል።

“እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአሁኑ ሰዓት ሙሉ ጤንነት ላይ እገኛለሁ” ሲል የገለጸው ጎሳዬ፣ ለማገገሙ የፈጣሪ እርዳታ፣ የቤተሰቦቹ እገዛ፣ የህክምና ባለሙያዎች ክብካቤ እንዲሁም በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ አድናቂዎቹ ያደረጉለት ጸሎት ትልቅ ሚና እንደነበረው ገልጿል።

በለንደን ቆይታውም በቃላት ሊገልጸው የማይችለውን ፍቅርና ድጋፍ ላሳዩት ወዳጆቹና አክባሪዎቹ በሙሉ ልባዊ ምስጋናውን አቅርቧል።

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ምኞቱን ገልጾ፣ ለመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች መልካም የፍልሰታ ጾም እንዲሆንላቸው ተመኝቷል።

“ሰላም ይስጠን!” በማለትም መልዕክቱን ቋጭቷል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: