የኒውክሌር ጦር መሳርያ የማስወገድ ታሪካዊ ጥሪ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፈረንጆቹ 1962 የኖቤል የሰላም ሽልማትን የተቀበሉት ታዋቂው አሜሪካዊ ኬሚስት እና የሰላም ተሟጋች ላይነስ ፖሊንግ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ማስወገድ አስደናቂ ንግግር አድርገው ነበር።

የኒውክሌር ጦር መሳርያ ማጥፋት ለሰብአዊ መብት እና ነፃነት መረጋገጥ መሠረታዊ እንደሆነ በንግግራቸው ላይ አጉልተው ገልጸው ነበር።

ፖሊንግ ጦርነትን ለማስቀረት የሚደረግ ጥረት ከሰው ልጅ ነፃነት እና ከግለሰቦች መብት መከበር ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው አፅንኦት ሰጥተው ነበር የተናገሩት።

የኒውክሌር እና አጠቃላይ የጦርነት አደጋ ከዓለም ሲወገድ በሁሉም ሀገራት የማህበራዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ስርዓቶች መሻሻል እንደሚታይና ይህም ለመላው የሰው ልጅ ጥቅም እንደሚያስገኝ እምነታቸው ነበር።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓን ሂሮሺማ እና ናጋሳኪ ላይ የተጣለው የአቶም ቦምብ ለፖሊንግ የህይወት አቅጣጫ መቀየር ምክንያት ሆነ።

ከሌሎች ታዋቂ የሳይንስ ሊቃውንት ጋር በመሆን የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን ውድድር ለማስቆም የተቋቋመውን እንቅስቃሴ እንዲመሰረት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ይህ ንቅናቄያቸው በ1995 የኖቤል ሰላም ሽልማት እንዲያሸንፉ አድርጓቸዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nobleprize #Pugwash
#Nuclear #atomicbomb
#LinusPauling #movement


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: