የኢትዮጵያና ስሪላንካ ወዳጅነት በኪነ-ጥበብ እና በወጣቶች ትብብር ሊያበብ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በኢትዮጵያ የስሪላንካ አምባሳደር ኒርማላ ኢንዱማቲ ዲያስ ፓራናቪታና ከኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ እና የትወና ዘርፍ ተወካዮች ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት በባህል ዲፕሎማሲ፣ በወጣቶች አቅም ግንባታ እና በደቡብ-ደቡብ ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

አምባሳደሯ ከአምሳ ሦስት በላይ የሰርከስ ትምህርት ቤቶችን ከሚወክለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርከስ ማህበራት ጥምረት (ENCAC) ፕሬዝዳንት አቶ ተክሉ አሻግሬ (ሄኖክ) ፣ ከ”ቢዮንድ ዳንስ ስቱዲዮ” የደንበኞች አገልግሎት ማኔጀር ሲና አምሳሉ እንዲሁም ከፍካት ሰርከስ አሰልጣኝና ቡድን መሪ አቶ ተመሰገን ግርማ ጋር ተከታታይ ውይይቶችን አድርገዋል።

​በውይይቱ ወቅት አምባሳደሯ የስሪላንካን ውብ የባህል ቅርስ በማስተዋወቅ የኢትዮጵያ ወጣት ከዋክብት በባህላዊ ውዝዋዜ፣ በቪዲዮ ትምህርቶች፣ በጉብኝቶች እና በባህል ፌስቲቫሎች የሚሳተፉበትን “ሪትም ኦፍ ላንካ” (Rhythm of Lanka) የተሰኘ መርሃ ግብር አስተዋውቀዋል።

በተጨማሪም በሰርከስና በውዝዋዜ ጥበብ ለተሰማሩ ወጣቶች የጋራ መድረኮችን በመፍጠር በዓለም አቀፍ ደረጃ አቅማቸውን የሚያሳዩበትና ተሞክሮ የሚለዋወጡበት ዕድል እንደሚመቻች ተገልጿል።

የድርጅቶቹ ተወካዮችም የተጀመረውን የትብብር ጥሪ በበጎ የተቀበሉት ሲሆን መርሃ ግብሩ የወጣቶችን አቅም ከማሳደግ ባለፈ የሁለቱን ሀገራት ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ተገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: