#Ethiopia | ሁለት የ17 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኬንያውያን ተማሪዎች ጎጂ የአየር ብክለትን ለመቀነስ የሚያስችል “ሄዋሳፊ” የተሰኘ አነስተኛ ዋጋ ያለው የመኪና ጭስ ማጣሪያ ፈጠሩ።
ይህ ማጣሪያ እንደ የበቆሎ ቆብ እና የኮኮናት ቅርፊት ካሉ የግብርና ተረፈ ምርቶች እንዲሁም ከስፒሩሊና አልጌ የተሰራ ሲሆን ዋጋውም 125 የአሜሪካ ዶላር ገደማ በመሆኑ ከሌሎች መሰል ምርቶች ጋር ሲነፃፀር እጅግ ርካሽ ያደርገዋል።
በናይሮቢ የህዝብ ማጓጓዣ ባሶች ላይ በተደረገው የጎዳና ላይ ሙከራ ማጣሪያው ጎጂ የሆኑ ጥቃቅን ቅንጣቶችን በ93.3 በመቶ የካርቦን ሞኖክሳይድ ልቀትን በ42 በመቶ መቀነስ የቻለ ሲሆን የተወሰነ የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠንንም መያዝ ችሏል።
ይህ አዲስ የፈጠራ ስራቸው የ”ዘ እርዝ ፕራይዝ” የአፍሪካ ቀጠና አሸናፊ ያደረጋቸው ሲሆን ፕሮጀክቱን የበለጠ ለማሻሻልና ተጨማሪ ሙከራዎችን ለማድረግ የሚያስችል የ12,500 ዶላር ሽልማት አግኝተዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.