#Ethiopia | በአሜሪካ ሚኒሶታ ዩኒቨርስቲ የዘር ማጥፋት ጥናት ተመራማሪ እና ዳሬክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ከጋዛ ጦርነት ጋር በተያያዘ ከሰጡት ሃሳብ ጋር በተያያዘ ከስራቸው ተነስተዋል።
ዶ/ር ራዝ ሴጋል በሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ የዘር ማጥፋት ጥናት ተመራማሪና ዳይሬክተር ሆነው እንዲሰሩ በቅጥር ኮሚቴው ሙሉ ድምፅ ተመርጠው እየሰሩ ባለበት ሁኔታ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ስራቸውን ባልተጠበቀ ሁኔታ ሰርዞት ነበር።
ፕሮፌሰሩ በፈረንጆቹ 2023 ባሳተሙት የጥናት ውጤቻቸው ላይ እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን ወታደራዊ እርምጃ የዘር ማጥፋት ወንጀል መሆኑን ገልጸው ነበር።
ይህ አቋማቸው ከእስራኤል የመብት ተሟጋች ቡድኖች ደጋፊዎች እና የህግ አውጪዎች ዘንድ የከፋ ተቃውሞና ጫና ማስከተሉ ተከትሎ ዩኒቨርሲቲው የስራ ውሏቸውን አቋርጧል።
የአሜሪካ የዲሞክራሲያዊ መብቶች አስጠባቂ ማዕከል ዶ/ር ሴጋልን በመወከል ዩኒቨርስቲው ላይ ክስ መስርቶ ነበር።
ክሱ የህዝብ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የሜኒሶታ ዩኒቨርሲቲ የወሰደው እርምጃ የፕሮፌሰሩን ህገ መንግስታዊ የመናገር መብት እና አካዳሚያዊ ነፃነት የሚጥስ ነው ሲል ተከራክሯል።
ከሁለት ዓመት የህግ እና የሰነድ ክርክር በኋላ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመሄዱ በፊት 250,000 ዶላር ካሳ ለፕሮፌሰሩ በመክፈል ክሱን ለማቋረጥ ተስማምቷል ሲል የፃፈው ዘ ጋርዲያን ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Usa #university
#Professor #Genocide
#Holocaust
Source: GetuTemesgen









No comments yet.