#Ethiopia | የምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች እ.ኤ.አ በ2030 ኤችአይቪ/ኤድስን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት የገቡትን ቃል ቢያድሱም የዓለም አቀፍ ለጋሾች ድጋፍ በፍጥነት መቀነስ ከፍተኛ ስጋት ደቅኖበታል።
እ.ኤ.አ በ2025 ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ ድጋፍ በ18 በመቶ የቀነሰ ሲሆን ከአሜሪካው ፔፕፋር የሚደረገው ድጋፍ መታገድ ብቻ በአፍሪካ ከ1,700 በላይ የሕክምናና አገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንዲዘጉ አድርጓል።
ቀጠናው አዳዲስ በበሽታው የመያዝ እና ከኤድስ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሞቶች በመቀነስ በኩል ትላልቅ ድሎችን ያስመዘገበ ቢሆንም የሀገር ውስጥ በጀት በአስቸኳይ ካልተመደበ የተገኘው ስኬት ወደኋላ ሊመለስ እንደሚችል ዩኤንኤድስ አሳውቋል።
በዚህም ምክንያት አፍሪካውያን መንግስታት የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽን በራሳቸው በጀት እንዲሸፍኑ ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው ይገኛል ዋናው ጥያቄ ግን ቫይረሱ ሳይስፋፋ መንግስታት በፍጥነት መንቀሳቀስ ይችላሉ ወይ? የሚለው ነው።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.