ዶ/ር ደረጀ እንግዳ አዲሱ የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​“በማህበረሰብ ውስጥ ነን!” በሚለው መሪ ቃሉ የሚታወቀውና በትምህርት፣ በምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ግንባር ቀደም የሆነው አንጋፋው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ርክክብ ፈጸመ።

​ላለፉት ሰባት ዓመታት ዩኒቨርሲቲውን በዕውቀትና በትጋት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ የፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸውን ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ለዶ/ር ደረጀ እንግዳ አስረክበዋል።

ዶ/ር ጀማል በቆይታቸው ለተቋማዊ ዕድገትና ለላቁ ስኬቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና የተቸራቸው ሲሆን፣ ወደፊት በሚሰማሩበት ማንኛውም መስክ መልካም ዕድል ተመኝቶላቸዋል።

​ይህንን ከፍተኛ ሀገራዊ አደራ የተቀበሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በጀመረው የራስ-ገዝነት የሽግግር ጉዞ ተቋሙን ወደ ላቀ የስኬት ማዕረግ ያሸጋግሩታል የሚል ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: