#Ethiopia | የዓለማችን አንጋፋው ሀገር መሪ የሆኑት የካሜሩን ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ ለሁለት ወራት ያህል ከህዝብ እይታ ርቀው መቆየታቸው በሀገሪቱ አነጋጋሪ ሆኗል።
ፕሬዚዳንቱ ባለፈው ሰኔ 7 ቀን “ለአጭር ጊዜ የግል እረፍት ወደ አውሮፓ” ማቅናታቸውን የቤተ መንግስት ጽህፈት ቤት አስታውቆ የነበረ ቢሆንም እስካሁን ወደ ሀገራቸው አልተመለሱም።
የካሜሩን የመንግስት ቃል አቀባይ ሬኔ ኢማኑኤል ሳዲ እሁድ ዕለት ለፈረንሳይ አር.ኤፍ.አይ በሰጡት አስተያየት “ፕሬዚዳንቱ በህይወት አሉ” ሲሉ ገልጸው በቅርቡ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ አስታውቀዋል።
የካሜሩን ገዢ ፓርቲ የፕሬዚዳንት ፖል ቢያ ከሀገር መራቅ ያሳደደረውን ስጋትና እየጨመረ የመጣውን ውቀሳ ተከትሎ ባለፈው ወር የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ አካሂዶ ነበር።
ከ1982 ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የቆዩት ፖል ቢያ ከዚህ ቀደምም ረጅም ጊዜያት ከሀገር ውጭ ማሳለፍ የተለመደ ባህሪያቸው እንሆነ ተገለጿል።
ግን አሁን ላይ የገጠማቸው የዕድሜ መገፋት ሀገር የመምራት ብቃታቸው ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንዲፈጠር አድርጓል።
አሁን ያደረጉት የውጭ ሀገር ጉዞም ከእስከዛሬዎቹ ረጅሙ እንደሆነ ተገልጿል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Cameron #president
#PualBiya #RFI
Source: GetuTemesgen







No comments yet.