ለሚስ ወርልድ ኢትዮጵያ የባህልና ጥበባት አምባሳደር ሞዴል ሩት ይርጋለም ሸኝት ተደረገላት።

- Advertisement -
Sidebar AD

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ መድረክ ለምትወክለው ሞዴል ሩት ይርጋለም የእንኳን ደስ አለሽና የሽኝት መርሃ ግብር አደረገ።

ክብርት ሸዊት ሻንካ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ለሞዴሏ መልካም ምኞታቸውን በመግለፅ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ በማስተዋወቅ በድል እንድትመለስ ተመኝተዋል።

​ክብርት ሸዊት በንግግራቸው ሞዴሏ የባህል አምባሳደር ሆና ከተሾመች በኋላ የሀገሪቱን ብዝሃ ባህላዊ ዕሴቶች በቅርበት ለመረዳት በተለያዩ ቦታዎች ጉብኝት ማድረጓን አንስተዋል።

በዚሁ መሠረት በደቡብ ኢትዮጵያ በመገኘት የህዝቡን ባህል፣ በአማራ ክልል ጎንደር በመሄድ የክልሉን ባህላዊ እሴቶች እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል ባሌ በመገኘት የገዳ ስርዓትንና ድቅ ተፈጥሮአዊ ሀብቶችን በበቂ ሁኔታ ጎብኝታለች ብለዋል።

​ይህ በክልሎች ያደረገችው ቆይታ የሀገሪቱን ባህልና ጥበብ ጠልቃ እንድታውቅ የረዳት ሲሆን፣ ከ130 በላይ የዓለም ሀገራት ሞዴሎች በሚሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያን በብቃት ለማስተዋወቅና ገጽታዋን ከፍ ለማድረግ እንደሚያግዛት ገልፀዋል።

​የገጠማትን ማንኛውንም ፈተና ተቋቁማ የሀገሯን ባህልና ጥበብ በዓለም አቀፍ አደባባይ ለማሳየት ቆርጣ የተነሳች ጠንካራ ወጣት በመሆኗ ትልቅ አድናቆትና ምስጋና እንደሚገባትም ክብርት ሸዊት ሻንካ አክለዋል።

ክብርት ሸዊት ​ለመላው ኢትዮጵያውያን ባስተላለፈው መልዕክት በመጪው ውድድር ላይ በሚፈጠረው የማህበራዊ ሚዲያ ማስፈንጠሪያ (Link) አማካኝነት ሁሉም ድጋፉን እንዲሰጥና ለሞዴሏ ስኬት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ሞዴል ሩት ይርጋለም በበኩሏ ለተደረገላት የሸኝትና መልካም ምኞት መርሀ ግብር ምስጋና አቅርባለች።

ሞዴሏ ሀገሯን በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለማስጠራት ቆርጣ እንደተነሳች በመግለፅ የገጠማት ችግር ወደሗላ እንደማይመልሳት አንስታለች።

ከዓለም አቀፉ ውድድር በሗላም በሀገሯ ያሉ ባህላዊና ጥበባዊ እሴቶችን ለማስተዋወቅ እደምሰራ ገልፃለች።

በመርሃ ግብሩ ላይ የክልልና የከተማ አስተዳደር የባህልና ስፖርት ሴክተር አመራሮች፣ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች፣ የሙያ ማህበራት አመራሮችና የሞዴሏ ቤተሰቦች ተገኝተው ለሞዴሏ የሀገር አደራ ተሰጥቷል።

Via የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: