በስለት እያስፈራሩ የሞባይል ስልክ የቀሙ 3 ወንጀል ፈፃሚዎች በእስራት ተቀጡ።

- Advertisement -
Sidebar AD

ሳሙኤል ደሳለኝ፣ ዮሴፍ መስፍን እና ዳግም አድነው የተባሉ ወንጀል ፈፃሚዎች ሐምሌ 6 ቀን 2018 ዓ/ም በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ሁለት ሰዎችን በስለት በማስፈራራት ሞባይል ስልካቸውን ቀምተው ይሰወራሉ፡፡

ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ/ም ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አንፎ ሮም ሰፈር ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ተመሳሳይ ወንጀል ሲፈፅሙ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል፡፡

የቤተል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንዲመሰረትባቸው ያደርጋል፡፡

የወንጀል ፈፃሚዎችን ጉዳይ ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን የወንጀል ችሎት ሳሙኤል ደሳለኝ እና ዮሴፍ መስፍን በ4 አመት ዳግም አድነው በ2 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።

Addis Ababa police



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2