‎የኢትዮጵያ የትምባሆ ቁጥጥር ዳሽቦርድ ይፋ ተደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የትምባሆ ምርቶችን ጎጂነት ለመግታትና በዘርፉ የሚከናወኑ የሕግ ማስከበር ሥራዎችን በመረጃ ላይ የተመሠረቱ ለማድረግ ያለመው የትምባሆ ቁጥጥር ዳታ ኢኒሼቲቭ ዳሽቦርድ ይፋ ሆኗል።

‎የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ፣ የጤና፣ ልማት እና ፀረ-ወባ ማኅበር እንዲሁም የመቋሚያ የማኅበረሰብ ልማት ድርጅት በጋራ በመሆን ባዘጋጁት በዚህ መድረክ ላይ፣ የትምባሆ አጠቃቀምንና የኢንዱስትሪዎችን ተፅዕኖ ለመግታት መረጃን በአንድ ማዕከል ማሰባሰብ ወሳኝ እርምጃ መሆኑ ተመልክቷል።

‎​ይህ አዲስ የተበገገው ዳሽቦርድ በተለይም መረጃዎችን በሀገራችን የሥራ ቋንቋ በአማርኛ አካቶ ማዘጋጀቱ መረጃው ለፖሊሲ አውጪዎች ብቻ ሳይሆን ለሚዲያዎች፣ ለተመራማሪዎችና ለሰፊው ሕብረተሰብ ያለ ምንም የቋንቋ መሰናክል በቀላሉ እንዲደርስ ያስችላል።

‎በውስጡም የትምባሆ ተጠቃሚነት ስርጭትን፣ የሕገ-ወጥ ንግድ ሁኔታዎችን እንዲሁም ታክስ በጤና እና በሀገር ገቢ ላይ የሚያመጣውን አወንታዊ ተፅዕኖ የሚያሳዩ አገራዊ የምርምር ውጤቶችን ያካተተ ነው።

‎ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች ከትምባሆ ሱስ የሚላቀቁበትንና ከምልሰተ-ሱስ የሚጠበቁበትን መንገድ የሚያመቻቹ መረጃዎች በውስጡ ተካተውበታል።

‎የትምባሆ ኢንዱስትሪዎችን የተቀናጀ እንቅስቃሴ በወቅቱ ለመቆጣጠር መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የማዘመን፣ ዳሽቦርዱን እስከ ታችኛው የመዋቅር ደረጃ ድረስ የማድረስና አቅም የመገንባት ሥራዎች በቀጣይ ትኩረት እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

ባለድርሻ አካላትም ይህንን ዝግጁ መረጃ በመጠቀም ሕግ የማስከበር፣ የግንዛቤ ማስጨበጥ እና ተጨማሪ የምርምር ሥራዎችን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ቀርቧል።

‎#TobaccoControl #PublicHealthEthiopia #EFDA #TDI #TobaccoDataInitiative #HealthDevAntiMalaria






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1