‎በንባብ ባህል ንቅናቄ ከ24.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተደራሽ መደረጉን ተገለፀ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎* የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ክልሎች እውቅና ተሰጥቷል

‎#Ethiopia | ​የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ባለፈው በጀት ዓመት ያከናወናቸውን አበይት ተግባራት የገመገመበትንና የቀጣይ የሦስት ዓመታት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ የመከረበትን ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ሴክተር ጉባኤ ተካሄደ።

‎በጉባኤው ላይ የተገኙት የባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ክብርት ሸዊት ሻንካ እንደገለጹት፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሕግ፣ በፖሊሲ እንዲሁም በባህልና ስፖርት ልማት ዘርፎች በርካታ አመርቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

‎ከእነዚህም መካከል ከ28 ዓመታት በኋላ የጸደቀው አዲሱ የስፖርት ፖሊሲና የትግበራ ማዕቀፍ፣ አዲሱ የስፖርት አዋጅ፣ የጥበባትና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ እና የጥበብ ምክር ቤት ደንብና መመሪያዎች መዘጋጀታቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ።

‎እነዚህ የፖሊሲ ማሻሻያዎች የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ፣ የስፖርት ኢኮኖሚውን በማጠናከርና በዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመቀረፍ ረገድ ጉልህ ድርሻ ይኖራቸዋል።

‎​በተጨማሪም በባህል ዘርፍ 52 አገር አቀፍ፣ ሃይማኖታዊና የብሔር ብሔረሰቦች የዘመን መለወጫ ክብረ በዓላት በሰላም የተከበሩ ሲሆን፣ ከ46 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በመሳተፉ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር አስችሏል።

‎የንባብ ባህልን ለማስፋፋት በተደረገው አገር አቀፍ ንቅናቄ ከ24.9 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተደራሽ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፣ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 454 ቤተ-መጻሕፍትን የማጠናከር ሥራ ተከናውኗል።

‎በኪነ ጥበቡ ዘርፍም የ”ኪን ኢትዮጵያ” ቡድን ሀገራዊ ባህልን ሲያስተዋውቅ፣ የሰርከስ ጥበብ ደግሞ 12 ዓለም አቀፍ ክብረወሰኖችን በመስበር ሀገርን ያስጠራበት ዓመት ነበር።

‎በስፖርቱ መስክ ደግሞ 49 ሺህ ታዳጊዎች በ1,550 የስልጠና ጣቢያዎችና በ36 ማዕከላት ስልጠና እየወሰዱ ይገኛሉ፤ የመንግሥት ልዩ ትኩረት ያረፈባቸው ትላልቅ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ስታደየሞች ግንባታም ወደ መጠናቀቁ ተቃርቧል።

‎​በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቀጣይ ዓመት ተቋማዊ ሪፎርምን በተሟላ መንገድ በመተግበር አገልግሎቶችን በዲጂታል ሥርዓት ለማዘመን ማቀዱ የተገለጸ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ግለሰቦች እና ተቋማት እውቅና ተሰጥቷል።

‎በዚህም መሠረት በባህልና ኪነጥበብ ዘርፍ
1. ‎የአማራ ባህል ቱሪዝም ስፖርት ቢሮ
2. ‎የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ
3. ‎አዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ

‎በስፖርት ዘርፍ
1. ‎የኦሮሚያ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
2. ‎.የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ
3. ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስፖርት ቢሮ ተሸላሚ ሆነዋል።

‎እንዲሁም ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከአራቱ ተጠሪ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ጸረ አበረታች ቅመም ባለስልጣን የልዩ ተሸላሚነት እውቅና አግኝተዋል።

‎ጌትነት ተመስገን
‎📷 ከበደ መክብብ

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ
‎#MinistryOfCultureAndSport
‎​#EthiopiaMoCS ​#Ethiopia ​#EthiopianNews






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2