“A new Ethiopian star is born; her name is Almaz Yohannis አዲስ የኢትዮጵያ ኮከብ ተወለደች፤

- Advertisement -
Sidebar AD

“A new Ethiopian star is born; her name is Almaz Yohannis አዲስ የኢትዮጵያ ኮከብ ተወለደች፤ ስሟም አልማዝ ዮሐንስ ነው” የተባለላት አትሌት ከአትሌት በላይነህ ዲንሳሞ፣ ቱርቦ ቱሞ እንዲሁም ከአትሌት ሳሙኤል ፍሬው የትውልድ ሀገር ሲዳማ የተገኘች አትሌት ናት።

ከዚያ ምድር በዚህ ዕድሜ፣ በአለም አደባባይ የሀገሯን ስንደቅ ከፍ የምታደርግ አትሌት እንደምትገኝ ማን አስቦ ኖሯል? Maganu galatamo አለች አፏን በፈታችበት በሲዳሙ አፎ። ለዛሬ አማርኛ ይቅርታ ያድርግልኝ ብላ ቃለ መጠይቋን ልብ በሚነካ የደስታ ስሜት ውስጥ ሆና በሲዳምኛ ገለፀችው። ቀጥላም ባሳለፈችበት የአትሌቲክስ ሕይወት ገና በጠዋቱ አቅሟን አይቶ ለዚህ ታላቅ ገድል ያጫትን አሰልጣኝ ሳሙኤል በቀለን አመሰገነች። ሳሙኤል በቀለ ከዛሬ አሥራ ስምንት ዓመት በፊት በጎዋ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት መምህር የሥራ ባልደረባዬ ነበር። ሳሙኤል በቀለ ከአርቤጎና ምድር ብዙ አትሌቶችን ያፈራ ነባር የአትሌትክስ አሰልጣኝ ነው። አልማዝ ቀጠለች ከሁላ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ አዱላንና እና አሰልጣኞዋን አሰፋ ጋዲሳን አመሰገነች። በቀጣይ የአትሌትክስ ሕይወቷ ኦሎምፒክ ማሸነፍ ህልሟ መሆኖዋንም ተናገረች። እንኳን Magano ረዳት። ሀሹ!!

Athlet Almaz Yohanis hawalle Maganu kaa’linohe!
Via: ሳሙኤል በላይነህ


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2