#Ethiopia | “በማህበረሰብ ውስጥ ነን!” በሚለው መሪ ቃሉ የሚታወቀውና በትምህርት፣ በምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት ግንባር ቀደም የሆነው አንጋፋው ጅማ ዩኒቨርሲቲ የአመራር ርክክብ ፈጸመ።
ላለፉት ሰባት ዓመታት ዩኒቨርሲቲውን በዕውቀትና በትጋት ሲመሩ የቆዩት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ የፕሬዝዳንትነት ኃላፊነታቸውን ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለነበሩት ለዶ/ር ደረጀ እንግዳ አስረክበዋል።
ዶ/ር ጀማል በቆይታቸው ለተቋማዊ ዕድገትና ለላቁ ስኬቶች ላበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ምስጋና የተቸራቸው ሲሆን፣ ወደፊት በሚሰማሩበት ማንኛውም መስክ መልካም ዕድል ተመኝቶላቸዋል።
ይህንን ከፍተኛ ሀገራዊ አደራ የተቀበሉት አዲሱ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው፣ ዩኒቨርሲቲው በጀመረው የራስ-ገዝነት የሽግግር ጉዞ ተቋሙን ወደ ላቀ የስኬት ማዕረግ ያሸጋግሩታል የሚል ትልቅ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.