ከነሀሴ 1-15
የሐዋርያትን ግብር ምሳሌ በማድረግ ልክ እንደ ሐዋርያት ለሐዋርያት የተገለጠ በረከት እና የእመቤታችን ረድኤት እንዲያድርብን ለሁለት ሳምንታት ሱባኤ የምንይዝባት ጾመ ፍልሰታን በልዩ መርሀ ግብር በቃጥላ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በመገኘት በሱባኤ እናሳልፍ።
ከነሀሴ 1-15 በሚኖረው ልዩ የትምህርተ ወንጌል መርሀ ግብር በእያንዳንዱ ቀን በርእሰ ጉዳይ ላይ ተመስርቶ ትምህርት ይሰጣል፤ በ14እናበ15 ከአንድ እስከ አስር ከህዝቡ ለተሰበሰበው ጥያቄ በመምህራን መልስ ይሰጣል። ስለሆነም የነፍስና የስጋ ጥያቄ በሚመለስባት፣ በየቀኑ የእመቤታችን ድንቅ ተአምራት በሚነገርባት በቃጥላ ጾመ ፍልሰታን ከሊቃውንቱ፣ ከመምህራኑ እና ከዘማርያኑ ጋር አብረን እናሳልፍ።
የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን!
የቤተክርሲያኒቱን የልማት ሥራዎች ለመደገፍ፡-
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000249446975
አባይ ባንክ አካውንት አካውንት ቁጥር 1641119233527011
አድራሻ:- ቦሌ አራብሳ፣ ከወረዳ 4 ገባ ብሎ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.