በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን

- Advertisement -
Sidebar AD

በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ወሰነ።

የተላለፈው መግለጫ ከዩቲዩብ እንዲወርድ እና ይቅርታ እንዲጠየቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።

ዐቃቤ ሕግ አርቲስቶቹ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ሚዲያ መግለጫ በመስጠታቸው የዋስትና መብታቸው ተነስቶ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉና ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል።

ዛሬ ነሀሴ 01 2018 ዓ/ም ጠዋት በነበረው ችሎት ተጠርጣሪ አርቲስቶቹ በጠበቆቻቸው አማካኝነት ለዐቃቤ ሕግ አቤቱታ በጽሑፍ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፣ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ ለምን መግለጫ እንደሰጡም ለችሎቱ የቃል ማብራሪያ አቅርበዋል።

አርቲስቶቹ በማብራሪያቸው ድርጊቱን የፈጸሙት በማኅበራዊ ሚዲያ ከሚደርስባቸው ስም ማጥፋትና መልካም ስም ከማጉደፍ ራሳቸውን ለመከላከል አስበው እንደሆነ አስረድተዋል።

ጉዳዩን መርምሮ ውሳኔ ለመስጠት ለከሰዓት 9:00 ሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፍርድ ቤቱ፤ በፍርድ ቤት በተያዘ ጉዳይ ላይ መግለጫ መስጠትና ማብራሪያ ማቅረብ ጥፋት መሆኑን አመልክቷል።

በማኅበራዊ ሚዲያ ለሚጠፋ ስም መልስ ለመስጠት እንኳን ቢሆን ድርጊቱን ፈጽሟል የሚሉትን አካል በሕግ መጠየቅ ሲገባ መግለጫ መስጠቱ ተገቢ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

ሆኖም «በጥቃቅን ጥፋቶች የዋስትና መብትን ማገድ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም» ሲል ዐቃቤ ሕግ የተከሳሾች የዋስትና መብት ተነስቶ በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል።

በተጨማሪም አርቲስቶቹና ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት ድርጊቱን ሆን ብለው የፈጸሙት በመሆኑ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 457 መሠረት እንዲቀጡ፣ ወይም በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ እንዲመሠረትባቸው ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም።

በዚህም መሠረት መግለጫ የሰጡት አርቲስቶች ሌላ ጊዜ ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጽሙ በከባድ ማስጠንቀቂያ እንዲታለፉ ውሳኔ ተሰጥቷል።

በሌላ በኩል «እግረኛው» በተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ እንዲተላለፍ ያደረገው አቶ ተክለሃይማኖት አዳነ ቪዲዮውን ከዩቲዩብ (YouTube) ላይ እንዲያወርድና ይቅርታ እንዲጠይቅ ፍርድ ቤቱ አዟል።

የመደበኛው የሕግ ሂደት ቀጠሮ ለጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም የተቀጠረ መሆኑ ታውቋል።

ገዛ ጌታሁን



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: