#Ethiopia | ለኮፕ 32 ዝግጅት በሙሉ አቅሙ መዘጋጀቱን የገለፀው የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ሙያተኞች ማኅበር “” በሚል መሪ ቀል 2ኛውን የዕውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ይፋ አደረገ።
ኢትዮጵያ በቅርቡ ለምታስተናግደው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ስኬታማነት የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ሙያተኞች ማኅበር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ መግባቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ ገልፀዋል።
አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ ይህ ታላቅ ዓለም አቀፍ መድረክ በኢትዮጵያ መካሄዱ የአገሪቱን ገጽታ ለመገንባት እና በቱሪዝም ዘርፉ ያለውን አቅም ለዓለም ለማስተዋወቅ ከፍተኛ እድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል።
በመሆኑም ወደ አገራችን የሚመጡ እንግዶችን በከፍተኛ ኢትዮጵያዊ እንግዳ ተቀባይነት ባህል ለመቀበል በሆቴልና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እና ስልጠና ማጠናቀቃቸውን አረጋግጠዋል።
የአዲስ አበባ ሆቴል እና ቱሪዝም ሙያተኞች ማኅበር የሦስት ዓመታት የሥራ ጉዞውን በማስመልከት “” በሚል መሪ ቃል 2ኛውን የዕውቅና እና ሽልማት ፕሮግራም ይፋ አደረገ።
ማኅበሩ ይፋ ባደረገው የጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለጸው ይህ መርሃ ግብር በሴክተሩ ውስጥ የሚታዩ አበይት ስኬቶችን ለማበረታታት የሥራ አፈፃፀምና የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥ የተዘጋጀ ነው።
የማኅበሩ ፕሬዚዳንት አቶ አሸናፊ ሙሉጌታ ለሆቴል ባለቤቶች ለቱሪዝም ኤጀንሲዎች ለትምህርት ተቋማት ለልማት አጋሮች እና ለብዙኃን መገናኛ አካላት ጥሪ በማቅረብ በዚህ ታሪካዊ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የዘርፉን ዕድገትና ልሕቀት በአንድነት እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
በዕለቱ በ4 ዋና ዋና ዘርፎች ሥር ከ25 በላይ ሽልማቶች እና ዕውቅናዎች እንደሚሰጡ ገልጸዋል።
የዕውቅናና ሽልማት ፕሮግራሙ
በግል ሙያዊ ብቃት፣ በምግብና መጠጥ ዝግጅት፣ በስራ አመራርና ደንበኞች አገልግሎት የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ሙያተኞች የሚበረከት ይሆናል።
እንዲሁም በሥራ ፈጠራ፣ በዘመናዊ አሠራር፣ በሆቴልና በኢቨንት አዘጋጅነት ብቁ የሆኑ ተቋማትም ይገኙበታል።
በአካባቢ ጥበቃና በማህበረሰብ ልማት ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ማህበራትና ተቋማት የሚበረከት ይሆናል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#ኢትዮጵያ #አዲስአበባ
#ሆቴል #ቱሪዝም #ማህበር



Source: GetuTemesgen








No comments yet.