ሞሃመድን ከእንግሊዝ ይልቅ ቱርክ ተቀብላዋለች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የግብጹ ኮከብ ሞሃመድ ሳላህ በሊቨርፑል የነበረውን ዘጠኝ ዓመታት የቆየ የጨዋታ ጊዜ በማጠናቀቅ የቱርኩን ክለብ ትራብዞንስፖር በይፋ ተቀላቅሏል።

የ34 ዓመቱ አጥቂ ከቱርኩ ክለብ ጋር ለሁለት ዓመታት የሚቆይ ውል የተፈራረመ ሲሆን በዓመት 17 ሚሊዮን ዩሮ ደመወዝ የሚያገኝ ይሆናል።

በተጨማሪም በስሙ ከሚሸጡ ልዩ ልዩ ምርቶች የ20 በመቶ የገቢ ድርሻ የሚያገኝበት አሰራር የተመቻቸለት ሲሆን ይህም ሳላህን የክለቡና የቱርክ ሱፐር ሊግ ዋና ገጽታ ለማድረግ የተወጠነ የንግድ ስምምነት ነው።

​በስታዲየም ተገኝተው ደመቅ ያለ አቀባበል ላደረጉለት በሺዎች ለሚቆጠሩ የትራብዞንስፖር ደጋፊዎች ንግግር ያደረገው ሳላህ በህይወቱ ገጥሞት የማያውቅ ድንቅ ፍቅርና አቀባበል እንደተደረገለት በመግለጽ ደጋፊዎቹን አመስግኗል።

በሊቨርፑል በነበረው ቆይታ በ442 ጨዋታዎች 257 ግቦችን በማስቆጠር ሁለት የፕሪሚየር ሊግ እና አንድ የቻምፒየንስ ሊግ ዋንጫዎችን ያሸነፈው ሞ፣ አሁንም ከአዲሱ ክለቡ ጋር ዋንጫዎችን በማንሳት አዲስ የስኬት ምዕራፍ ለመጻፍ እንደሚጫወት ገልጿል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: