ሞተር ብስክሌት በመጠቀም የቅሚያ ወንጀል የፈፀመው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ዳግም ሙላት የተባለው ተጠርጣሪ ሞተር ብስክሌት በመጠቀም የቅሚያ ወንጀሉን የፈፀመው ሀምሌ 30 ቀን 2018 ዓ/ም በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ልዩ ቦታው ጎሮ ትምህርት ቤት አካባቢ ከቀኑ 5፡00 ሠዓት ነው፡፡

የግል ተበዳይ አብዱልከሪም አማን መንገድ ላይ ቆመው ታክሲ በሚጠብቁበት ወቅት ተጠርጣሪው የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-7850 አ/አ ሞተር ባይስክል እያሽከረከረ ከኋላቸው በመምጣት 100ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ ስልክ ቀምቶ ከአካባቢው ለመሰወር ሲሞክር በህብረተሰቡና በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን በቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የሰፈራ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

አብዛኛው የሞተር ብስክሌት አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በማክበርና ወንጀልን ለመከላከል የበኩላቸውን ድጋፍ እያደረጉ ቢገኙም መሰል ግለሰቦች መኖራቸውን በመረዳት ህብረተሰቡ ንብረቱ ላይ በቂ ጥንቃቄና ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅለይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል ፡፡


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: