#Fastmereja:-በስደት ሀገር ከነበረ ከባድ የህይወት ውጣ ውረድ እና የእስራት ፈተና በመውጣት በጠንካራ ማንነቷ የራሷን ስኬት መገንባት የቻለችው ስራ ፈጣሪ ሱመያ ዋሪስ፣ በሀገሯ አዲስ የንግድ ምዕራፍ መጀመሯን በዛሬዉ እለት አስታወቀች።
በስደት ሀገር በሰው ቤት ተቀጣሪነት በመጀመር፣ በኋላም በሊባኖስ ዋና ከተማ በትንሽ የሴቶች ውበት ሳሎን ተነስታ ታዋቂ የሂውማን ሄር (Human Hair) አስመጪ መሆን የቻለችው ሱመያ፤ የማህበራዊ ሚዲያ (ቲክቶክ) አጠቃቀሟ እና ከአርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ የተደረገላት ድጋፍ ለስኬቷ ትልቅ መንገድ መክፈቱን ገልጻለች።
በጉዞዋ ላይ ባጋጠማት ድንገተኛ የእስራት ፈተና ላለፉት 10 ዓመታት የደከመችበትን ሀብትና ንብረት ብታጣይም፣ ወደ ሀገሯ ኢትዮጵያ ከተመለሰች በኋላ በፈጣሪ እርዳታ፣ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ባሉ ኢትዮጵያውያን፣ በወዳጇ ሀቢባ እንዲሁም በአርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ ያልተቋረጠ ደጋፊነት መልሳ መቆም እንደቻለች ገልፃለች።
ድምጻዊ እና አርቲስት ቬሮኒካ አዳነህ ለሱመያ ዋሪስ ባደረገችላት ትልቅ ሰርፕራይዝ፣ ለ«ሱሱ ሂውማን ሄር» (Susu Human Hair) ለሁለት ዓመታት ያህል ያለ ምንም ክፍያ በነፃ የብራንድ አምባሳደር ሆና ለመስራት ተስማምታለች።
በተጨማሪም ሱመያ ዋሪስ በሀገሯ ኢትዮጵያ ግዙፍ የሂውማን ሄር መሸጫ እና ዘመናዊ የውበት ሳሎን ለመክፈት ዝግጅቷን ያጠናቀቀች ሲሆን፣ ጥራት ያላቸውን የፀጉር ምርቶች በቀጥታ ከቻይና ግዙፍ የሂውማን ሄርኩባንያዎች ጋር በመስራት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ላይ መድረሷ ተገልጿል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ በድጋሚ ለመክፈት ዝግጅቷን ማጠናቀቋን እንዲሁም ከቻይና ሂውማን ሄር ኩባንያ ጋር አብራ መስራት መጀመሯን አክላ አስታውቃለች።
ወደፊትም ተደራሽነቷን በማስፋት በተለያዩ ሀገራት የተለያዩ ቅርንጫፎችን የመክፈት እቅድ እንዳላትም ነዉ የገለፀችዉ።



Source: FastMereja









No comments yet.