#Ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት የሚገዙ በርካታ ሰዎች የካርታ ስም ለማዞር ወደ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዳደር ቢሮዎች በሚያመሩበት ወቅት ቀድመው ያላሰቡትና ያልተደገሰላቸው ከፍተኛ ወጪ ከፊታቸው እንደሚጠብቃቸው አያውቁም።
ገዢዎች የመንግስትን የስም ማዛወሪያ ታክስ እና ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ገና ከጅምሩ ከግምት ውስጥ ካላስገቡ፣ የያዙትን የገንዘብ እቅድ ሙሉ በሙሉ በማበላሸት ለከፍተኛ የፋይናንስ ኪሳራና ስጋት እንደሚዳረጉ የንብረት ባለሙያው አቶ ዮሴፍ ያሳስባሉ።
አንድን ቤት እንደተገዛ ወዲያውኑ የሚፈለገው የ 6.5 በመቶ ክፍያ የሚሰላው ገዢዎች እንደሚያስቡት በውላቸው ላይ በተጻፈው ዋጋ ብቻ ሳይሆን መንግስት ባወጣው የቦታ ዝቅተኛ ተመን እና በውሉ ዋጋ መካከል ከፍ ባለው ላይ ተመስርቶ ነው።
ይህ ክፍያ የ 4 በመቶ አሹራ ወይም የስም ዝውውር፣ የ 2 በመቶ የቴምብር ቀረጥ እና የ 0.5 በመቶ የአደጋ ጊዜ ፈንድ ስብስብ ሲሆን፣ ለምሳሌ በ10 ሚሊዮን ብር ቤት ለገዛ ግለሰብ ከቤት ዋጋው ውጭ 650 ሺህ ብር ተጨማሪ ዝግጁ ገንዘብ ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛውም የቤት ገዢም ሆነ የሪል እስቴት አልሚ ከግዢ ውል በፊት እነዚህን ማጠናቀቂያ ወጪዎች አብሮ ያካተተ ትክክለኛ የፋይናንስ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት ተገልጿል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.