#Ethiopia | በ21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች (U20) የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ሁለተኛ ቀን በተካሄዱ የማጣሪያ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አስደሳች ውጤት በማስመዝገብ ለፍፃሜ ውድድር ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በወንዶች 1500 ሜትር ውድድር በብቸኝነት ኢትዮጵያን የወከለው ደስታው ታዴ 3:43.03 በሆነ ጊዜ ምድቡን አራተኛ በመጨረስ ለፍፃሜ ውድድር አልፏል።
በሴቶች 1500 ሜትር ውድድር ደግሞ ሁለቱም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች የተሳካ ውጤት አስመዝግበዋል። ሀረገወይን ካላዩ 4:12.54 በሆነ ጊዜ በምድብ ሁለት ሁለተኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ኤልሳቤት አማረ 4:18.24 በሆነ ጊዜ ምድብ ሶስትን በቀዳሚነት በማጠናቀቅ ለፍፃሜ መድረስ ችላለች።
በዚህም ደስታው ታዴ፣ ሀረገወይን ካላዩ እና ኤልሳቤት አማረ በፍፃሜው ውድድር ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ለማስመዝገብ ይፎካከራሉ።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.