🙏
የፍልሰታ ጾም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፍልሰቷንና ክብሯን በማሰብ የሚጾም የጸሎት፣ የንስሐ፣ የምልጃና የምሕረት ጾም ነው። ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን ያመለክታል። በእነዚህ የተቀደሱ ቀናት ምእመናን በጾም፣ በስግደት፣ በጸሎትና በምጽዋት በመትጋት የእግዚአብሔርን ምሕረት ይለምናሉ፤ “እምነት ያለው ሥራ ይኑረው” እንዲል ቃሉ፣ ጾም ከምጽዋት ጋር ሲታጀብ በፊቱ የተወደደ መሥዋዕት ይሆናል።
“ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም” በከባድ ንፋስና ዝናብ ምክንያት ቤተ መቅደሱ ፈርሶ ይገኛል፣ መነኮሳቱም በድርቅና በርሃብ ከባድ ፈተና ውስጥ ናቸው።
መሬቱ ደርቋል፣ ከጸሎት መልስ የሚቀመስ እህል ጠፍቷል፣ መነኮሳቱ በረሃብና በችግር እየተፈተኑ የዕለት ሕይወታቸውን ለመግፋት በእጅጉ ተቸግረዋል።
የምግብ እጥረት ችግር በየቀኑ እየበረታባቸው ነው። ይህ የእነርሱ ብቻ ፈተና ሳይሆን የሁላችንም ፈተና ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ (1ኛ ቆሮንቶስ 12፥26) ላይ፡- «አንድም ብልት ቢሰቃይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሰቃያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል» ይላል፡፡በዚህ ምዕራፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እያንዳንዱ ምእመን የአንዱ መከራ የሁሉም መከራ፣ የአንዱም ክብር የሁሉም ደስታ መሆኑን ያስተምራል።
ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ጾም ከምጽዋትና ከርኅራኄ እንደማይለይ ታስተምረናለች፡፡እግዚአብሔርም፦ “የምወደው ጾም ይህ አይደለምን?… ለተራበ እንጀራህን መቁረስ፣ ድሆችንም ወደ ቤትህ ማስገባት ነው።” ይላል (ኢሳይያስ 58፥6–7) ። በዚህ ቅዱስ ወቅት የጾማችን ፍሬ በምጽዋትና በፍቅር ሥራ ሊገለጥ ይገባል።
“በጎ ማድረግንና መለገስን አትርሱ፤ እንዲህ ያለውን መሥዋዕት እግዚአብሔር ይወዳልና።”(ዕብራውያን 13፥16) እንዲል ቃሉ፤በዚህ የፍልሰታ ጾም የጸሎታችንን ፍሬ በምጽዋት እናሳይ፤ ለቤተ መቅደሱ መልሶ መገንባት፣ ለመነኮሳቱ ምግብና መሠረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት በአቅማችን እንረባረብ።
ዛሬ የምንሰጠው ትንሽ ድጋፍ የተራበን ያጸናል፣ የፈረሰውን ያቆማል፣ በልባቸው ተስፋን ያበራል። እንግዲህ በዚህ የተቀደሰ የፍልሰታ ጾም ወቅት በጸሎት፣ በምጽዋትና በፍቅር ሥራ አንድ እንሁን፤ ገዳማዊያኑን ስንደግፍ እኛም የበረከቱ ተሳታፊ እንሆናለንና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡- 1000766349227
አቢሲንያ ባንክ ፡- 262281132
ለበለጠ መረጃ:- 0944672222 ወይም 0916106921



Source: FastMereja








No comments yet.