የሳይንስ ድንበር የለሽነት አደጋ ላይ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ኦማር ያጊ የምዕራባዊያንን የቪዛ ፖሊሲ አጥብቀው ተቹ።

በኬሚስትሪ ዘርፍ ባበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦ የኖቤል ሽልማት ባለቤት የሆኑት ታዋቂው ሳይንቲስት ኦማር ያጊ በአሜሪካ እና በአውሮፓ ሀገራት እየተተገበሩ ባሉ ከባድ የቪዛ ገደቦች ላይ ጠንካራ ትችት ሰንዝረዋል።

ምሁሩ ባስተላለፉት መልዕክት አሁን ላይ በጣም እየጠበቁ የመጡት የቪዛ ፖሊሲዎች የሳይንስ የዕድገት ወሰን እየገደቡት ይገኛሉ ብለዋል።

ጥብቅ የቪዛ መስፈርቶች በተለይም ከታዳጊ ሀገራት የሚመጡ ወጣት ሳይንቲስቶች ተመራማሪዎችና ተማሪዎች በዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችና በከፍተኛ የጥናት መድረኮች ላይ እንዳይሳተፉ ትልቅ እንቅፋት እየሆኑባቸው ይገኛል ብለዋል።

ሳይንስና ምርምር ፍሬ የሚያፈሩት በተለያዩ ሀገራት ያሉ ሊቃውንት ሀሳብና እውቀት ሲለዋወጡ እንጂ ድንበርና አጥር ሲበጅላቸው እንዳልሆነ ፕሮፌሰር ያጊ አብራርተዋል።

የምዕራባውያን ሀገራት የቪዛ ፖሊሲያቸውን ካላሻሻሉ ዓለም አቀፍ የሳይንስ እድገት እንዲቀጭጭ እና የጋራ ችግሮችን እንደ የአየር ንብረት ለውጥ እና ለአዳዲስ በሽታዎች መፍትሔ እንዳይገኝ ምክንያት ይሆናል ሲሉ አስጠነቅቀዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Usa #scientists
#European #visa
#policy #Nobelprize


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2