የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማገድ ለጊዘው እንዲቆም ተደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

የደንብ 557/2016 ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያ አስኪጸድቅ የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ማገድ ለጊዘው እንዲቆም ተደርጓል::

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማጅመንት ባለሰልጣን የደንብ ተላላፊዎችን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ መቀበልም ሆነ ሰሌዳ መፍታት ሳያስፈልግ የዲጂታል የትራፊክ ቁጥጥር እና ቅጣት ማስፈጸሚያ ሲስተም ስርዓት በመዘርጋት የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክን ለመቆጣጣር የወጣውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 557/2016 የቅጣት አወሳሰንን እየተገበረ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ከደንቡ ተግባር ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በደንብ መተላላፍ የነጥብ ጣሪያ ደርሰው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና እንዲወስድና እና ነጥባቸው ሳይሞላም አስቀድሞ ስልጠና ወስደው ነጥብ የሚቀንስላቸው ደንብ ተላላፊዎች በደንቡ አንቀፅ 96 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ በሁለቱም የእውቅና ክህሎት ስልጠና ወስደው የወሰዱበትን ማረጋጋጫ ሲያቀርቡ እግዱ እንደሚነሳ ይደነግጋል፡፤

ይሁን እንጂ ከአፈጻጸም አንጻር ይኸው አገራዊ ደንብ በሌሎች ክልሎች ተግባራዊ ባለመደረጉ እና በአዲስ አበባ ከተማ በሚያሽከረክሩ ደንብ ተላላፊዎች ላይ ብቻ መተግበሩ በደንብ ተላላፊዎች ዘንድ የፍትሀዊነት ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል፡፡

ባለሰልጣን መ/ቤቱም ይህንኑ የፍትሀዊነት ጥያቄ ለመንገድ ደህንነት ፈንድ አገልግሎት ባሳወቀው መሰረት አና ተቋሙም ችግሩን በመረዳት በቀን 23/11/2018 በቁጥር 1904/18 በተጻፈ ደብዳቤ ምላሽ ሰጥቶበታል፡፡

በምላሹም ከደንብ ትግበራ ጋር በተያያዘ ተደጋጋሚ ደንብ ተላላፊዎች የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃዳቸው ታግዶ የተሀድሶ ስልጠና የሚያገኙበትን ሂደት የተሳካ ለማድረግ መመሪያ ሲዘጋጅ መቆየቱን አመላክቷል፡፡

እንዲሁም መመሪያውም ያለበትን ሂደቶች አልፎ በአሁኑ ወቅት ለፍትህ ሚኒስቴር መላኩንና በሌሎች ክልሎችም ወጥ የሆነ አሰራር ለመዘርጋት ሲባል ለጊዜው የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃዱን የማገዱ ተግባር አንዲዘገይ በማለት አሳውቋል ፡፡

በመሆኑም የደንብ መተላለፉ የገንዘብ ቅጣቶቹ እንደተጠበቁ ሆነው ዝርዝር የአፈጻጸም መመሪያው ጸድቆ እስኪላክ ድረስ የትራፊክ ጉዳት ካደረሱ አሽከርካሪዎች ውጪ ለጊዜው በነጥብ እና በቆይታ /ሳይከፍል 6 ወር የቆየ/ ከዚህ በፊት የታገዱትም ሆነ በቀጣይ የሚታገድ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ መቆሙን ገልጿል፡፡ ከእግዱ መቆም በስተቀር ደንብ ተላላፊዎች ያሉባቸውን የቅጣት ክፍያ መክፈል እንደሚጠበቅባቸውም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1