የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ለተጨማሪ ዉጊያ እየተዘጋጁ መሆናቸዉ ተነገረ‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ታጣቂዎች ለተጨማሪ ዉጊያ የሚያደርጉት ዝግጅት መቀጠሉን የተለያዩ ወገኖች አስታወቁ።የአዉሮጳ የሰላም ተቋም መገናኛ ዘዴዎችንና ሌሎች ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበዉ የመቀሌና የአዲስ አበባ ግንኙነት ይበልጥ እየተበላሸ ነዉ።ሁለቱ ወገኖች የሚያደርጉት የጦር ኃይል ንቅናቄም ሌላ ጦርነት ሊጫር ይችላል የሚለዉን ሥጋት አንሮታል።ሁለቱ ወገኖች ልዩነታቸዉን ሰላማዊ፣ ሁሉን አካታችና ገንቢ በሆነ ዉይይት እንዲፈቱ ተቋሙ ጠይቋል።
የአይን ምሥክሮች በበኩላቸዉ የትግራይ ኃይል የሚባለዉ የታጣቂዎች ስብስብ በርካታ ተዋጊዎችን ወደ ምዕራብ ትግራይ እያዘመተ ነዉ።እንደሚሉት የትግራይ ተዋጊዎች ትግራይ ክልልን ከአፋርና ከአማራ ክልሎች ጋር በሚያዋስነዉ ድንበር አካባቢም ምሽግ እየቆፈሩ መሆኑንም የዓይን ምሥክሮች አስታዉቀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ባንፃሩ አማራና አፋር ክልሎች ከፍተኛ የወታደራዊ ንቅናቄ እያደረገ መሆኑን የዓይን ምሥክሮች ተናግረዋል።
ከአፋር ክልል በደረሰን መረጃ መሠረት በክልሉ የዞን አራት ተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች ተጨማሪ ወታደሮች ሠፍረዋል።ነዋሪዎቹ በሥም በዘረዘሯቸዉ ወረዳና ቀበሌዎች ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ማንቀሳቀሱና ተጨማሪ ኃይል ማስሩ እስከ ትናንት ማታ ድረስ ቀጥሎ ነበር።
@Seledadotio

No comments yet.