#Ethiopia | ላለፉት ስድስት ወራት በተለያዩ የወጣቶች ዲፕሎማሲና አመራር ስልጠና እንዲሁም ልምምድ ሲያካሂዱ የነበሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ 12 ወጣት አምባሳደሮች በዲፕሎማሲያዊ ፕሮቶኮል የሹመት ደብዳቤያቸውን በማስገባት በይፋ ተሾሙ።
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሆነ የሚነገረው ይህ የወጣት አምባሳደሮች የሹመት ስነ-ስርዓት ሀገሪቱ እየሄደችበት ላለችው ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ታምኖበታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በቅርቡ ሁለተኛው ዙር የወጣት ዲፕሎማሲና አመራር መርሃግብር የሚጀምር በመሆኑ ፍላጎቱ ያላቸው ወጣቶች ከአሁኑ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ የቀረበ ሲሆን፤ ለዚህም እድሜያቸው ከ18 እስከ 29 ዓመት የሆኑ፣ ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ወይም ከሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት ቤት (ከ11-12ኛ ክፍል) በትምህርት ቤታቸው ለዚህ አምባሳደርነት የተመረጡ፣ ወይም ደግሞ ከወጣት አደረጃጀቶችና ወጣት መር ተቋማት ተወክለው የሚመጡ ወጣቶች መወዳደር ይችላሉ።
በተጨማሪም በዲፕሎማሲ ሙያ ውስጥ የመግባት ፍላጎት ያላቸው እና የሴፍ ላይት ኢንሼቲቭ—የኢትዮጵያ ወጣቶች አመራርና ዲፕሎማሲ አካዳሚ የሚያዘጋጀውን የ30 ቀናት ቻሌንጅ ለመቀበል እንዲሁም የሴፍ ላይትን ራዕይ ለማስቀጠልና አብሮ ለመስራት የተዘጋጁ ተወዳዳሪዎች ተቋሙ የሚያዘጋጀውን የፅሑፍ ፈተና አልፈው ሲገኙ በስልጠናው ውስጥ በነፃ የሚካተቱ ይሆናል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.