ትልቅ ነገር ማድረግ ካልቻላችሁ ትንሽ ነገር በትልቅ ፍቅር አድርጉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia |በአለም ታሪክ ውስጥ ብዙ ሀያላን መሪዎች ፈላስፎች እና ታላላቅ ሰዎች ንግግር አድርገዋል።

ነገር ግን እንደ ማዘር ትሬዛ በለሰለሰ ድምፅ የዓለምን ልብ የነካ የታበዩትን ያሳፈረ እና ለተቸገሩት ተስፋ የሰጠ ስሜት ቀስቃሽ ንግግር ጥቂት ነው።

ማዘር ቴሬዛ በሰሩት ወደር የሌለው የመልካምነት እና የርህራሄ አገልግሎታቸው በ1979 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸንፈዋል።

ሽልማቱን ባሸነፉበት ወቅት ያደረጉት ታሪካዊ ንግግር ዛሬም ድረስ በሰው ልጅ ህሊና ውስጥ አዲስ ሆኖ ይደመጣል።

የሚል ታሪካዊ ንግግር አደረጉ።

የመልካምነትን እውነተኛ ትርጉም ለአለም ሁሉ አበሰሩ።

የዓለም ሰላም እንዲሰፍን እና መልካምነት እንዲኖር ምን እናድርግ ብሎ የጠየቃቸውን ሰው ሲመልሱ ወደ
ቤትህ ተመለስና ቤተሰብህን ውደድ ሲሉ ነበር የመለሱለት።

መልካምነት ከሩቅ ሳይሆን ከራሳችን
ከጎረቤታችን እና ከቅርብ ወዳጆቻችን ፈገግታ እንደሚጀምር በፅኑ አሳስበዋል።

ዛሬ የምታደርጉት መልካም ነገር ነገ ሊረሳ ይችላል ቢሆንም ግን መልካም ማድረጋችሁን ቀጥሉ።

የማዘር ቴሬዛ ይህ ታሪካዊ ንግግር የቃላት ስብስብ ብቻ ሳይሆን የተግባር ውጤት ነበር።

ህይወታቸውን በሙሉ በኮልካታ ጎዳናዎች ለወደቁት፣ ለታመሙት እና ለተረሱት አሳልፈው የሰጡት እናት ናቸው።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nobelprize #religion
#Mothorteresa #charity


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2