‎አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች መድረክ ተጠናቀቀ

- Advertisement -
Sidebar AD


#Ethiopia | ‎በአርባ ምንጭ ከተማ ሲካሄድ የቆየው አገር አቀፍ የሕግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ ተጠናቋል።

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጉባኤው ሰብሳቢ እና የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ቴዎድሮስ ምሕረት፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የተገልጋዮችን እና የኅብረተሰቡን እርካታ በጋራ ማረጋገጥ የመድረኩ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ገልጸዋው፤ በዚህ ጉዳይ ላይ በጋራ ሥልጣንና ኃላፊነት መሥራት በአዋጁ የተጣለብን የሁላችንም ኃላፊነት ሲሉ ተናግረዋል።

‎ክቡር ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከፍትሕ ተዳራሽነት እና ቀልጣፋነት ጋር በተያያዘ በጋራ በመምከር ለሕግ የበላይነት መረጋገጥ ነጻ እና ገለልተኛ ፍርድ ቤት የመፍጠር ኃላፊነት ከመድረኩ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

‎መድረኩ የጋራ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ለመመልከት ያስቻለ መሆኑን የጠቆሙት ክቡር ፕሬዝዳንቱ፤ እርስ በእርስ የሚያገናኙ ጉዳዮችን በማመቻቸት በተለይም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም በኩል በሁሉም ዘንድ የታየው ለውጥና የተገኘው ውጤት የሚያስደስት መሆኑን ገልጸዋል።

‎በመድረኩ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን የሚረዱ የተለያዩ ሐሳቦች ተነስተው ጥልቅ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፤ የድጎማ በጀት አከፋፈል ቀመር መመሪያ፣ የቃለ መሃላ አፈጻጸም ማስፈጸሚያ ማንዋል፣ እንዲሁም የቪዲዮ ኮንፈረንስ እና ኢ-ፋይሊንግ ማዕከላት አስተዳደር መግባቢያ ስምምነት ሰነዶች ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኃላ ጸድቀዋል።

‎በውሳኔው መሰረት የጸደቁ ሰነዶች የፊርማ ስነ ስርዓት የተካሄደ ሲሆን መድረኩ የታቀዱለትን ግቦች በማሳካት ተጠናቋል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2