ከአየር ላይ ገዳይ ተፎካካሪነት ወደ ወንድማማችነት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia| የሰው ልጅ በጠላትነት ውስጥም ቢሆን ሰብአዊነትንና ወዳጅነትን ማበጀት እንደሚችል ለዓለም ያሳዩት የጦር አብራሪዎች።

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ በ1943 የሁለት ተቃራኒ ሀገራት አብራሪዎች በሰማይ ላይ የተገናኙበት አስደናቂ አጋጣሚ ተፈጥሮ ነበር።

አሜሪካዊው ወጣት አብራሪ ቻርሊ ብራውን በ B-17 ቦምብ ጣይ አውሮፕላኑ በጀርመን ላይ ጥቃት ፈጽሞ ሲመለስ አውሮፕላኑ በጠላት ሀይል በከባዱ ተመታ።

የአውሮፕላኑ ሞተር ተበላሽ የቡድኑ አባላት ክፉኛ ቆሰሉ አውሮፕላኑም ለመውደቅ ተቃረበ።

በዚያው ቅጽበት የጀርመን የአየር ኃይል ጀግና የነበረው ፍራንዝ ስቲግለር በጀርመኑ ሜሰርሽሚት ተዋጊ አውሮፕላኑ ወደ አየር ተከሰተ።

ፍራንዝ ወደ አሜሪካውያኑ አውሮፕላን ሲቀርብ የተገደሉትንና የቆሰለውን ቻርሊ ተመለከተ።

ስቲግለር የቆሰለና ያልታጠቀን ጠላት መግደል ውርደት ነው በሚል መርህ
አውሮፕላኑን ከመተኮስ ይልቅ ከጎናቸው አብሮ እንዲበር አደረገ።

የጀርመን የፀረ አውሮፕላን ተኳሾች እንዳይመቷቸው ከለላ አደረገላቸው።

ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ሁለቱም በሕይወት ተረፉ።

ቻርሊ ብራውን በዚያች አስፈሪ ቀን ሕይወቱን ያደነውን የጀርመን አብራሪ ማንነት ለማወቅ ለአሥርት ዓመታት ሲፈልግ ቆየ።

በመጨረሻም በፈረንጆቹ 1990 ከ47 ዓመታት በኋላ ቻርሊ በጋዜጣ ላይ ባወጣው የማስታወቂያ ጥሪ ምክንያት ሁለቱ የቀድሞ ጠላቶች ተገናኙ።

ፍራንዝ በወቅቱ ወደ ካናዳ ተዛውሮ ይኖር ነበር።

ሲገናኙ የቀደመው የጦርነት ቅሬታና የሀገር ጠላትነት ሙሉ በሙሉ ወደ ጎን በመተው ፍቅራቸውን ተለዋወጡ።

ከዚያች ቀን ጀምሮ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ እንደ ወንድማማች ኖሩ።

በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ የሰላም፣ የሰብአዊነት እና የይቅርታን አስፈላጊነት ማስተማር ጀመሩ።

ሁለቱም በጥቂት ወራት ልዩነት ውስጥ በተፈጥሮ በሽታ ምክንያት ከዚህ ዓለም ተለዩ።

በጦርነት ውስጥ ጠላት የነበሩት እነዚህ ሰዎች ከፖለቲካ በላይ የሆነውን የሰው ልጅ ሰብአዊነት አስቀደሙ።

የሰው ልጅ በጠላትነት ውስጥም ቢሆን ሰብአዊነትንና ወዳጅነትን ማበጀት እንደሚችል እነዚህ ጓደኛሞች ለዓለም አሳይተዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#worldwar #America
#German #friendship #CharlieBrown
#FranzStigler


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: