የስኬት ባንክ አጠቃላይ ሀብት በ51 በመቶ በመጨመር 29 ቢሊዮን ብር ደረሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ስኬት ባንክ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን በመገምገም እና በ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለመምከር ያዘጋጀውን ዓመታዊ የሥራ አመራር ጉባኤ ዛሬ ነሐሴ 2 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል።

በመድረኩ የቀረበው የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑን 10.3 ቢሊዮን ብር ማድረስ የቻለ ሲሆን የተከፈለ ካፒታሉን ደግሞ ወደ 7.9 ቢሊዮን ብር አሳድጓል።

በተጨማሪም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 14.7 ቢሊዮን ብር የተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል።

በእነዚህ እና በሌሎች የባንክ አገልግሎቶች በበጀት ዓመቱ 4.1 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ገቢ በማግኘት ከታክስ በፊት ከ1.54 ቢሊዮን ብር በላይ ማትረፍ የቻለ ሲሆን፣ ይህም አጠቃላይ የሀብት መጠኑን በ51 በመቶ በማሳደግ ወደ 29 ቢሊዮን ብር አድርሶታል።

የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዳምጠው አለማየሁ በበጀት ዓመቱ የተመዘገበው ውጤት አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።

አያይዘውም በ2019 በጀት ዓመት የባንኩን ተወዳዳሪነት የበለጠ ለማጠናከር፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን ለማስፋፋት እና ለደንበኞች የሚሰጡ የአገልግሎት አማራጮችን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስትራቴጂካዊ ዕቅዶች ተነድፈው ወደ ሥራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል።

በጉባኤው ማጠቃለያ በበጀት ዓመቱ ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዲስትሪክቶች፣ ቅርንጫፎች እና ሠራተኞች የዋንጫ እና የምስክር ወረቀት ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል።

ስኬት ባንክ የስኬትዎ መሠረት።

#siketbank #ethiopianbanking #finance #ethiopianeconomy #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1