#Ethiopia | የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) የመሥራች እና የመጀመሪያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር ጥላሁን እስማኤል ካሳሁን ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን ተከትሎ የከፍተኛ አመራር ሽግግር ማድረጉን ዛሬ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሠረት የገበያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ወይዘሮ ዮዲት ካሳን አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርጎ በመሾም ተቋሙን ወደ አዲስ መሪ አድርጎ ሰይሟል።
የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ የማኔጅመንት አባላት እና ሠራተኞች ዶክተር ጥላሁን እስማኤል የኢትዮጵያን የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከምሥረታው ጀምሮ በማቋቋምና ጠንካራ መሠረት በመጣል ረገድ ላሳዩት ቁርጠኝነትና የላቀ አመራር ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ለወይዘሮ ዮዲት ካሳ እንኳን ደስ አለዎት ብላሏቸዋል ፤ በአዲሱ የኃላፊነት ሚናቸው የሀገሪቱን የካፒታል ማርኬት ዕድገት ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሩታል ተብሎ ይጠበቃል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.