#Ethiopia | በሳይንሱ አለም ውስጥ “አምላክ የለም” በሚለው አቋማቸው ለረጅም ዓመታት ይታወቁ የነበሩ ነገር ግን በህይወታቸው ማብቂያ ወይም በምርምር ዘመናቸው ማጠቃለያ ላይ ፈጣሪ መኖሩን የመሰከሩ አያሌ ናቸው።
እነዚህ ተመራማሪዎች የዲ.ኤን.ኤን እና የቁስ አካልን ውስብስብነት ሲረዱ ከዚህ ሁሉ ነገሮች ጀርባ አንድ ሀይል አለ እሱም ፈጣሪ ነው ወደሚል ድምዳሜ ደርሰው አልፈዋል።
እነዚህ ተመራማሪዎች አቋማቸውን ሲቀይሩ በሳይንሱና በፍልስፍናው ዓለም ውስጥ ትልቅ አነጋጋሪ ሁኔታን ፈጥረው ነው የምድር ቆይታቸውን ያጠናቀቁት።
ከእነዚህ ተመራማሪዎች መካከል እንግሊዛዊው ፈላስፋና ተመራማሪ አንቶኒ ፍሉ ዋነኛው ነው።
አንቶኒ ለግማሽ ክፍለ ዘመን ከ50 ዓመታት በላይ”አምላክ የለም” ለሚለው አስተሳሰብ ዋና አቀንቃኝና በርካታ መጻሕፍትን የጻፉ ሰው ነበሩ።
በህይወታቸው ማጠቃለያ አካባቢ አቋማቸውን በይፋ በመቀየር በሳይንስ ዓለም ትልቅ ድንጋጤን ፈጠሩ።
እኚህ ተመራማሪ በህይወታቸው ማብቂያ አካባቢ”There is a God” አምላክ አለ የሚል መጽሐፍ ጽፈው አሳተሙ።
የትኛውም ሳይንሳዊ መረጃ ቢኖረኝ ማስረጃው ወደ ሚመራኝ ቦታ እከተላለሁ በማለት አለምን የፈጠረ አንድ አምላክ መኖሩን አምነው አልፈዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#philosophy #science
#Superintellect #religion
#Superpower #AlmightyGod
Source: GetuTemesgen








No comments yet.