የፈጠርነው የኔቶ ታናሽ ወንድም ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የቱርክ፣ ፓኪስታን እና ሳዑዲ ዓረቢያ የጋራ መከላከያ ስምምነት ከኔቶ አንቀጽ 5 ጋር ተመሳሳይ መሆኑ ተገለጸ።

የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን እንደገለጹት ቱርክ ከፓኪስታን እና ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር የፈረሙት የጋራ የመከላከያ ስምምነት በቴክኒክ ደረጃ ከኔቶ አንቀጽ 5 ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አስታወቁ።

የኔቶ አንቀጽ 5 በአንድ አባል ሀገር ላይ የሚሰነዘር ጥቃት በሁሉም አባላት ላይ እንደተሰነዘረ ይቆጠራል የሚል የጋራ መከላከያ መርህን የያዘ ነው።

ሚኒስትር ሀካን ፊዳን በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት እና በቱርክ መካከል የተደረሰው ስምምነት አባል ሀገራቱን ከውጭ ጥቃት በጋራ ለመከላከል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ስምምነቱ የተደረገው አንድን ሀሠገር ለማጥቃት ወይም ለአንድ ሀገር የታለመ እንዳልሆነ ጠቆመዋል።

አባል ሀገራቱ ጥቃት እስካላደረሱ ድረስ ማንኛውም አካል የጥቃት ኢላማ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም ብለዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Nato #Article5
#defensepact #Turkey
#pakistan #Saudi


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: