#Ethiopia | የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ በጀመሩት አምስት የፌደራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2019 የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።
የተማሪዎች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር የጠቆመው ሚኒስቴሩ፣ የምዝገባ መስፈርቶችን፣ የተወሰነውን ጊዜ እና ሌሎችንም ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ በይፋ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጻል።
በመሆኑም ፍላጎቱ ያላቸው ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠባበቁና የትምህርት ሚኒስቴርን ኦፊሴላዊ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እንዲከታተሉ ጥሪ አስተላልፏል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.