በፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ሊጀምር ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የትምህርት ሚኒስቴር በ2018 የትምህርት ዘመን ሥራ በጀመሩት አምስት የፌደራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለ2019 የትምህርት ዘመን ተጨማሪ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ።

​የተማሪዎች ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር የጠቆመው ሚኒስቴሩ፣ የምዝገባ መስፈርቶችን፣ የተወሰነውን ጊዜ እና ሌሎችንም ዝርዝር መረጃዎች በቀጣይ በይፋ ይፋ እንደሚያደርግ ገልጻል።

በመሆኑም ፍላጎቱ ያላቸው ተማሪዎች፣ ወላጆች እና አሳዳጊዎች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠባበቁና የትምህርት ሚኒስቴርን ኦፊሴላዊ የመረጃ ማሰራጫ መንገዶች እንዲከታተሉ ጥሪ አስተላልፏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: