የእግዜር ድልድይ

- Advertisement -
Sidebar AD

“ዓይናችን እያየ በሳይንስ ሊብራራ የማይችል ተአምር እየኖርን ነው”

“ድልድዩ በምድር ህግ ፈርሷል በሰማይ ህግ ግን አሁንም ጸንቶ ቆሟል!”

#Ethiopia | በግሪክ ቴሳሊ ከተማ የሚገኘው የተደረመሰ ጥንታዊ ድልድይ አጠቃላይ የፊዚክስ ህግጋትንና ሳይንሳዊ ግምቶችን በመጣስ ለመላው አለም አስገራሚና አነጋጋሪ ክስተት ሆኗል።

በፈረንጆቹ 2023 በከተማው በተከሰተውና ከፍተኛ ውድመት ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በቴሳሊ የሚገኘው ዋና ድልድይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተደርምሶ ነበር።

በወቅቱ በነበረው የጎርፍ ኃይል የተነሳ የድልድዩ የመሃል ምሰሶዎችና ዋናው መዋቅር ተሰባብረው የወደቁ በመሆናቸው መሀንዲሶችና የአካባቢው ባለስልጣናት ድልድዩ ከጥቅም ውጪ ሆኗል ማለፍም ፍጹም ሞትን መጋበዝ ነው ሲሉ ወዲያውኑ አግደውት ነበር።

የአካባቢው አስተዳደር ችግሩን ለመቅረፍና የትራፊክ ፍሰቱን ለማስቀጠል ሲል በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት የተሰራ አዲስና ዘመናዊ ድልድይ ጎን ለጎን ገንብቶ ለምርቃት አብቅቷል።

ነገር ግን ያልተጠበቀውና መላውን ህዝብ ያስገረመው ክስተት የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።

አሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ አስተማማኝና ጥንካሬ ያለው ተብሎ የተሰራውን አዲሱን ድልድይ ከመጠቀም ይልቅ ፍርስራሹንና በግማሽ የተደረመሰውን አሮጌ ድልድይ መጠቀማቸውን መርጠዋል።

በየቀኑ በሰው ልጅ እይታ “አሁኑኑ ይናዳል” ተብሎ የሚጠበቀው ይህ የተሰበረ ድልድይ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖችንና ከባድ ተሽከርካሪዎችን ያለምንም አደጋ በሰላም ማሳለፉን ቀጥሏል።

የአካባቢው ነዋሪዎችና አሽከርካሪዎች ድልድዩ በምንም ዓይነት የምህንድስና ስሌት ሊቆም የማይችልበት ደረጃ ላይ ሆኖ ሳለ ፍጹም ሳይወድቅ ሰዎችን ማሻገሩን ሲያዩ ተገርመው አላቆሙም።

አሽከርካሪዎቹ “በዚህ ድልድይ ስናልፍ ልዩ የሆነ ጥበቃና ሰላም ይሰማናል” በማለት አዲሱን መንገድ ትተው በአሮጌውና በተሰበረው ድልድይ ላይ መሻገራቸውን ቀጥለውበታል።

ይህ የምህንድስና ውጤት ሳይሆን በእግዚአብሔር እጅ የተደገፈ ተአምር በማለት የእግዜር ድልድይ የሚል ስም ሰጥተውታል።

በግሪክ ቴሳሊ የሚገኘው ይህ “የእግዜር ድልድይ” በአሁኑ ወቅት የበርካታ ጎብኚዎችና የጋዜጠኞች ትኩረት መሳቢያ ከመሆኑም በላይ በሳይንሳዊ ስሌትና ሊብራራ ባልቻለ ተአምራዊ ጥንካሬው መካከል ያለውን ድንበር በመጣስ በዓለማችን አነጋጋሪ ከሆኑ አጋጣሚዎች አንዱ ሆኖ ቀጥሏል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Ethiopia #GetuTemesgen #GetuNews
#Greece #tesale
#Collapsed #Bridge
#Palaiopyrgos


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2