ለመጀመር ምን እስኪሟላልህ እየጠበክ ነው?

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ዕድሜ ቁጥር ብቻ መሆኑን በተግባር ያረጋገጡት የ75 ዓመቱ አዛውንት ታታይ ሩበን አቤላ፣ የ21 ኪሎ ሜትር የግማሽ ማራቶን ሩጫን በ1 ሰዓት ከ56 ደቂቃ ብቻ በማጠናቀቅ ድንቅ ታሪክ ፈጽመዋል።

ይህንን ስኬታቸውን ያስመዘገቡት በዘመናዊና ውድ የካርቦን ሩጫ ጫማዎች ወይም ውድ የሆኑ የስፖርት ትጥቆችን በመጠቀም ሳይሆን ለብዙ ማይሎች ሲያገለግሏቸው በቆዩት አሮጌና ያረጁ ጫማዎቻቸው እንደነበር ተገልጿል።

​የታታይ ሩበን የላቀ ውጤት ምስጢር የለበሱት ጫማ ሳይሆን ለብዙ አሥርታት ያዳበሩት ከፍተኛ የዲሲፕሊን ባህል፣ ወጥነት ያለው ጥረት እና የማይበገር የሥነ ልቦና ጥንካሬ ነው።

ብዙ ሰዎች አንድን ነገር ለመጀመር ፍጹም የሆነ ጊዜን፣ የተሟላ ቁሳቁስን ወይም ምቹ አጋጣሚን በሚጠብቁበት በዚህ ወቅት ታታይ ሩበን ታላቅነት የሚጀምረው ሁኔታዎችን ሳይጠብቁ በመጀመርና ውሳኔ በማድረግ እንደሆነ በተግባር አስመስክረዋል።

ይህ የአዛውንቱ የፅናት ጉዞ ለብዙዎች ትልቅ ትምህርትና አነሳሽነትን የፈጠረ ሲሆን “ለመጀመር ምን አንዲሟላሎት እየጠበቁ ነው?” የሚል ጥያቄንም ያስነሳል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2